Jimma University Open access Institutional Repository

በጅማ ከተማ የቁባ አባ አረቡ የመውሊድ በአል ስርአተ-ከበራ ሂደት ትንተና

Show simple item record

dc.contributor.author ዘይነባ ሸረፋ
dc.contributor.author ማንያለው አባተ
dc.date.accessioned 2021-01-22T12:56:47Z
dc.date.available 2021-01-22T12:56:47Z
dc.date.issued 2011-12
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/5256
dc.description.abstract ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ የቁባ ኣባ አረቡ የመውሊድ ክብረ በአል ስርዓተ ክዋኔ ሂደት ትንተና ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፤ የጥናቱ ዋና ዓላማ የቁባ አባ አረቡ የመውሊድ በአል ስርአተ-ከበራ (ከዚያራ እስከ ፍጻሜው) ያለውን ሂደት መተንተን ነው፡፡ አላማውን ለማሳካት ጥናቱ በገላጭ የምርምር ስልት በመመርኮዝ የተከናወነ ሲሆን፤ ያነሳቸው የምርምር ጥያቄዎችም (1) የቁባ አባ አረቡ የመውሊድ ስርዓተ ክዋኔ ምን ይመስላል? (2) በመውሊድ ስርዓተ ክዋኔው ላይ የሚቀርቡት ቃላዊ ግጥሞች ክዋኔ እና ክብረ በዓሉን አጅበው የገቡ ቁሳዊ ባህሎች ከሐይማኖታዊ ገጽታቸው ባሻገር ምን አይነት ፎክሎራዊ ገጽታ አላቸው? የሚሉ ጥያቄዎች በጥናቱ ለመመለስ ተሞክሮዋል፡፡ አላማ ተኮርና የጓድ ጠቆም የንሞና ዘዴን በመጠቀም የጥናቱ አካባቢና ናሙናዎች ምርጫ የተከናወነ ሲሆን፤ ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በምልከታ፣ ቃለ መጠይቅ እና በተተኳሪ የቡድን ውይይት በመሰብሰብ በአውዳዊ ወይም ክዋኔ ተኮር ንድፈ ሀሳብ የተደገፈ ትንተናና ማብራሪያ ቀርቧል፡፡ በጥናቱ ግኝቶች መሰረት፤ የመውሊድ በአሉ ክዋኔ የየራሳቸው ዓላማ ያላቸው ሁነቶች ድምር ውጤት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከጥናቱም የተገኘው ውጤት የቁባ አባ አረቡ የመውሊድ ክብረ በዓል ከዋናው ዋዜማ በፊት በወንዶችና ሴቶች መውሊድ ስርአተ ክዋኔዎች የሚጀምር ሲሆን ዋናው የዋዜማ ቀን ደግሞ ረቢያል አወል 11 ሌሊት ለ12 መንጊያ ነው፡፡ በመውሊድ በአሉ የአከባበር ስርዓት ላይ የተስተዋሉት የክዋኔ ሁነቶች ዚያራ፣ ዱአ (ምርቃት)ና መንዙማ ናቸው፡፡ የነዚህ ሁነቶች አጠቃላይ መጠሪያ ‹‹ዱአይ›› እንደሚባልና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ሁነቶች በስፋት የተንጸባረቁበት እንደሆነ ጥናቱ ቃኝቷል፡፡ ከዚሁ ጎን የታዩት የመንዙማ ግጥሞች በተከወኑበት የክዋኔ ሒደት አንጻር በሁለት መንገድ (በድቤ እና በእንጉርጉሮ) እንደሚባሉ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን፤ የመውሊድ ስርዓተ ክዋኔን አጅበው የገቡትን ቁሳዊ ባህሎች ከአሰራራቸውና ጠቀሜተቸው አንጻር በሶስት መልኮች (ቃላዊ ግጥሞቹን አጅበው የሚገቡ፣ የመመገቢያና ጌጣጌጥ) እንደሚፈረጁ ጥናቱ ተመልክቷል፡፡ እነዚህን ቁሶች ማህበራዊ፣ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ጉዳይ ጋር ግንኙነት ያላቸውና የተፈጥሯዊና ተለጣፊ እሴት፣ ታሪክ ነቃሽነት፣ ተወካይነትና ውስንነት ሆነው ገጽታ እንዳላቸው ጥናቱ ቃኝቷል፡፡ የቁባ ኣባ አረቡ የመውሊድ ክብረበአል ተግባርም የማጠናከር፣ የማምለጥና ማህበረሰቡን የመቆጣጠር ተግባር ያለው ከመሆኑ አንጻር ይህ መንፈሳዊ፣ ታሪካዊና ቁሳዊ ባህል ማህበረሰቡን ከማስተዋቅ አንጻር ያለው ፋይዳ ቀላል ባለመሆኑ ጥበቃ ቢደረግለት የሚል አስተያየት ተሰጥቷል፡፡ en_US
dc.language.iso en en_US
dc.title በጅማ ከተማ የቁባ አባ አረቡ የመውሊድ በአል ስርአተ-ከበራ ሂደት ትንተና en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account