dc.contributor.author | እንድሪስ, አወል | |
dc.contributor.author | ለማ, ንጋቱ | |
dc.date.accessioned | 2021-12-29T12:49:29Z | |
dc.date.available | 2021-12-29T12:49:29Z | |
dc.date.issued | 2012-08 | |
dc.identifier.uri | https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/5981 | |
dc.description.abstract | ጥናቱ የቤንች ብሄረሰብን የህይወት ሽግግር ስርዓት ርዕዮተዓለምን መመርመር ትኩረት አድርጎ የተካሄደ ነው፡፡ ጥናቱ አይነታዊ የአጠናን ዘዴን ተከትሎ የተካሄደና በገላጭ የጥናት ንድፍ የተቀነበበ ነው፡፡ መረጃዎች በምልከታ፣ በቃለ መጠይቅ፣ በቡድን ውይይት እና በሰነድ ፍተሻ አማካኝነት የተገኙ ናቸው፡፡ በጥናቱ የተሳተፉ ሰዎችም በዋናነት የተመረጡት በአላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ስልት ሲሆን በአጋዥነት የጥቆማ ስልትም ግልጋሎት ላይ ውሏል፡፡ ከልደት፣ ከጉርምስናና ከቁንጅና፣ ከጋብቻና ከሞት ጋር የተያያዙ የብሄረሰቡ የህይወት ሽግግር ርዕዮተ አለማዊ ፍልስፍናን የሚገልጹ መረጃዎች ከክዋኔያዊ፣ ከአውዳዊና ከተግባራዊ ትወራ ማህቀፍ አንፃር በገላጭ የመረጃ መተንተኛ ስልት ተተንትነው ቀርበዋል፡፡ ትንተናውም የተካሄደው የህይወት ሽግግር ምዕራፎችን /መለየት፣ ሽግግር/ ለውጥና መጠቃለልን መሰረት ባደረገ መልኩ ነው፡፡ እንዲሁም በሽግግሩ ወቅት አብረው የሚመጡ የብሄረሰቡ መንፈሳዊ፣ ቃላዊና ቁሳዊ ጉዳዮች ትዕምርት ከማህበረሰቡ ርዕዮተ አለማዊ ፍልስፍና አንፃር ተፈክሯል፡፡ ከትንተናውም በመነሳት የብሔረሰቡ የህይወት ሽግግር እረከኖች የማህበረሰቡን የህይወት መዋቅር፣ የማህበራዊና ተፈጥሯዊ ህይወት ድንበር መለያና መገለጫ ሲሆኑ እንዲሁም ቅድመ ማንነት መገለጫ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ በሽግግሩ ወቅት የሚሰተዋሉት የብሄረሰቡ ርዕዮተ አለማዊ ፍልስፍናዎች ደግሞ ራሱንና ተፈጥሮን የሚተረጉምበት/የሚረዳበት፣ ከሚያምነው እምነት ተነስቶ ነገን በዛሬ መነጽር የሚገልጽበት፣ የህይወት መመሪያው እና የማህበራዊ ህይወቱ መሰረት አድርጎ የኖረባቸው አስተሳሰቦችን ለመረዳት የሚያስችሉ መሆናቸው በጥናቱ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ከዚህም በመነሳት የህይወት ሽግግር ርዕዮተ አለማዊ ፍልስፍናዎች በብሄረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ሚና እንዳላቸው በመረዳት በቋሚነት ማክበርና ማስተላለፍ፣ ምንም እንኳ ባህል በባህሪው ተለዋዋጭ ቢሆንም ማህበረሰቡ በህይወት ሽግግረ ላይ ያለውን ርዕዮት ማስቀጠል የሚችልበትን ሁኔታ መፍጠሩ አስፈላጊ መሆኑን የሚጠቁሙ የይሁንታ ሀሳቦችን በመስጠት ጥናቱ ተቋጭቷል፡፡ | en_US |
dc.title | የህይወት ሽግግር ስርዓት ርዕዮተዓለማዊ ትንተና በቤንች ብሔረሰብ | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |