Jimma University Open access Institutional Repository

የአማርኛ አፈ-ፈት ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ አንቀጽ ሲጽፉ የሚፈጽሟቸው ሰዋስዋዊ ስህተቶች ትንተና (በአማራ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

Show simple item record

dc.contributor.author ተካቡ, ታደሰ
dc.contributor.author ተክሌ, ፈረደ
dc.date.accessioned 2021-12-29T13:05:20Z
dc.date.available 2021-12-29T13:05:20Z
dc.date.issued 2011-08
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/5983
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በአማርኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ በሚጽፏቸው አንቀጾች ውስጥ ሰዋሰዋዊ ስህተቶችን ተንትኖ መፈተሸ መቻል ነው፡፡ ተጠኚ ተማሪዎቹ በአማራ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን በጣረማበር ወረዳ በሶስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2011 ዓ.ም ይማሩ የነበሩ 1200 የዘጠነኛ ክፍል አማርኛ አፈ-ፈት ተማሪዎች ናቸው፡፡ የአጠናን ዘዴው ገላጭ የምርምር ዘዴን የተከተለ ሲሆን፣ መረጃዎቹ በአይነታዊና በመጠናዊ ተተንትነዋል፡፡ በጥናቱ የተካተቱት 120 ተማሪዎች ሲሆኑ፣ የተመረጡትም በቀላል የዕጣ ንሞና ዘዴ ነው፡፡ ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት በተጠኚ ተማሪዎቹ በሁለት ዙር 240 አንቀጾች እንዲጽፉ ተደርጓል፡፡ በእነዚህ አንቀጾች መሰረት ተማሪዎቹ የሚፈጽሟቸውን ስህተቶች ለመለየት ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በጠቅላይ ናሙና ከተመረጡት የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በቃለ-መጠይቆች መረጃ ተሰብስቧል፡፡ እነዚህ መረጃዎችን በመጠቀም ለተማሪዎች ስህተት መፈጸም ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ለመለየት ተችሏል፡፡ ከአንቀጾቹ ዕርማት በተገኘው መረጃ መሰረት ጠቅላላ የስህተቶች ብዛት 1020 ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 500 (49.01) የስነ ድምጽ ስህተት፣ 330 (32.36%) የስነ-ምዕላድ ስህተት እንዲሁም 190 (18.7%) የቃላት ድግግሞሽ ስህተት ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ከመምህራን በተገኙት መረጃዎች መሰረት የስህተቶቹ መከሰት ምክንያቶች የማስተማሪያ መሳሪያዎች ዝግጅት፣ የማስተማሪያ ዘዴና የስ-ነልቦናዊ ሁኔታዎች ተጽዕኖዎች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እነዚህን ችገሮች ለማቃለል የማስተማሪያ መሳሪያዎችን አዘገጃጀትና የማስተማሪያ ዘዴዎችን ማሻሻል፣ እንዲሁም ተማሪዎች የጽሑፍ ልምዳቸውን እንዲያዳብሩ መምህራን ለጽህፈት መልመጃዎች ትኩረት ሰጥተው ለተማሪዎቻቸው ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ የትምህርቱን ይዘቶች ከተመደበው ክፍለ ጊዜ ጋር እንዲጣጣም ማድረግ፣ የጽሑፍ ስራውን ከመምህራን ዕርማት በተጨማሪ ተማሪዎች እርስ በርሳቸው እንዲተራረሙ ማመቻቸት እንዲሁም መማሪያ መጽሐፉን መገምገም የሚሉ የመፍትሄ ሀሳቦች ተጠቁመዋል፡፡ en_US
dc.title የአማርኛ አፈ-ፈት ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ አንቀጽ ሲጽፉ የሚፈጽሟቸው ሰዋስዋዊ ስህተቶች ትንተና (በአማራ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማበር ወረዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት) en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account