Jimma University Open access Institutional Repository

የኦፖ ብሔረሰብ የለቅሶ ስርዓት ክወና ትንተና

Show simple item record

dc.contributor.author የሺ, መኮንን
dc.contributor.author ጌታቸዉ አንተነህ
dc.date.accessioned 2021-12-29T13:10:57Z
dc.date.available 2021-12-29T13:10:57Z
dc.date.issued 2012-09
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/5984
dc.description.abstract ይህ ጥናት በኦፖ ብሔረሰብ የለቅሶ ስርዓት ክወና ትንተና በሚል ርዕስ የቀረበ ሲሆን የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት በኦፖ ብሔረሰብ ዘንድ በድህረ ሞት ጊዜ ያለዉ የሀዘን እርዝማኔ፣ ስለሞት ያላቸዉ አመለካከት እና የለቅሶ ስርዓተ ክዋኔ በተለያዩ ምክንያቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለወጠ በመሄዱ ሙሉ በሙሉ ከመጥፋታቸዉ ወይም ከመለወጣቸዉ በፊት ተሰንደዉ አንዲቀመጡ በሚል ነዉ፡፡ የጥናቱ ዋና ዓላማ ደግሞ በኦፖ ብሔረሰብ የለቅሶ ስርዓት ክዋኔን መተንተን ነዉ፡፡ ዓላማዉን ለማሳካት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ማለትም የኦፖ ብሔረሰብ ስለ ሕይወትና ሞት ያለዉ እሳቤ ምን ይመስላል? የብሔረሰቡ የለቅሶ ስርዓት ሂደት ምን ይመስላል? በለቅሶ ስርዓቱ ወቅት የሚታዩ ትዕምርቶች ምን ምን ጉዳዮችን ያመለክታሉ? በኦፖ ብሔረሰብ የለቅሶ ስርዓት የሚታዩት መንታ ገጽታዎች ምን ይመስላሉ? የሚሉ ጥያቄዎች በጥናቱ ለመመለስ ተሞክሯል፡፡ ይህ ጥናት በገላጭ ዘዴ የተጠና ሲሆን ዓላማ ተኮር የንሞና ዘዴን ለመጠቀም ለጥናት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በምልከታ ፣ በቃለ መጠይቅና በተተኳሪ ቡድን ዉይይት የተሰበሰበ ሲሆን በክዋኔ ተኮር ፈለግና በመዋቅራዊ ንድፈ ሀሳብ ለመቃኘት ተሞክሯል፡፡ ከጥናቱም የተገኘዉ ዉጤት የኦፖ ብሔረሰብ ስለሞት ያለዉ እሳቤ ሕይወትና ሞት ከፈጣሪ የተሰጠ እንደሆነና አንድ ሰዉ ሞተ የሚባለዉ ልብና ሳንባ ሙሉ በሙሉ ስራቸዉን ሲያቆሙ እንደሆነ ከሞት በኋላም ሕይወት እንዳለ የሚያምኑ መሆኑን፣ የኦፖ ብሔረሰብ የለቅሶ ስርዓት ክዋኔ በማህበራዊ ደረጃ እና በዕድሜ የሚለያይ መሆኑ፣ በለቅሶ ስርዓት ክዋኔ የተለያዩ ትዕምርቶችን የሚጠቀሙ መሆናቸዉንና የተለያዩ መንታ ገጽታዎች ያላቸዉ መሆኑ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ በአንጻሩ የኦፖ ብሔረሰብ የለቅሶ ስርዓተ ክዋኔ በተለያዩ ኃይማኖታዊ አሰተምህሮቶችን የብሔረሰቡ አባላት እየተቀበሉ በመምጣታቸዉ በፊት የነበረዉ ክዋኔ እየተቀየረና እየተለወጠ በመምጣቱ በጊዜ ሂደት ሙሉ በሙሉ ሳይጠፉ እንዲሰነድና እንዲቀረስ ምሁራንና የባህሉ ባለቤቶች የድርሻቸዉን ቢወጡ መልካም ነዉ፡፡ en_US
dc.title የኦፖ ብሔረሰብ የለቅሶ ስርዓት ክወና ትንተና en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account