Jimma University Open access Institutional Repository

በሒደታዊ ዘውግ ማስተማር ዘዴ መፃፍንለማሻሻል ያለው ሚና በሠቃ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በኦሮምኛ አፈ-ፈት በሆኑ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author ዳባሽ ዮሐንስ
dc.contributor.author ጌታቸው ስዩም
dc.contributor.author አብይ አሠፋ
dc.date.accessioned 2021-12-30T07:12:03Z
dc.date.available 2021-12-30T07:12:03Z
dc.date.issued 2011-08-09
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/5990
dc.description.abstract ይህ ጥናት ሂደተ ዘውጋዊ የመፃፍ ማስተማሪያ ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂልን በማሻሻል ረገድ ያለውን ውጤታማነት ፈትሽዋል፡፡ ጥናቱም ተተኳሪ አድርጎ የተካሄደው በኦሮሚያ ክልል በጂማ ዞን በሠቃ ጮቆርሳ ወረዳ በሚገኘው ሠቃ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2011 ዓ.ም በሚማሩ በ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ ጥናቱም በፍትነታዊ ሙከራ ዘዴ ተማሪዎችን በቁጥጥር እና በሙከራ ቡድን ሁለት ክፍሎችን በመውሰድ ተካሂዷል፡፡ መረጃዎችም በፈተና እና በምልከታ የመረጃ መሰብሰብያ ዘዴዎች ተሰብስበዋል፡፡ በተደረገው አተገባበራዊ ክንውን የተገኘው መረጃ በመጠናዊና በአይነታዊ ዘዴን በመመስረት በገላጭ እስታቲክስ ስልት ተተንትነዋል፡፡ የተገኘውም ውጤት እንደሚያመለክተው በሂደታዊ ዘውግ የተማሩት የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች በልማዳዊው (በመርሃ ትምህርቱ) ከተማሩት የቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች በተሻለ የመጻፍ ክሂላቸው እንደተሻሻለ፣ በቂ ደረጃ ላይ እንደደረሰ፣ የመጻፍ ተሳትፎዋቸው እንደተሸሻለ፣ በመጻፍ እንደተደሰቱና የመጻፍ ጭንቀታቸው መካከለኛ መሆኑን አመልክቷል፡፡ በመሆኑም ሂደታዊ ዘውግ የመፃፍ ማስተማሪያ ዘዴን በመጠቀም የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂልን ማሻሻል፣ በቂ ደረጃ ላይ ማድረስ፣ ተሳትፎቸውን መጨመር፣ የመጻፍን ተግባር ደስተኛ ማድረግ እና የመጻፍን ጭንቀት በመቀነስ ተማሪዎችን ለደረጃቸው የሚመጥን የመጻፍ ክሂል ችሎታ ላይ ማድረስ ይቻላል የሚል አስተያየት ላይ ተደርሷል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title በሒደታዊ ዘውግ ማስተማር ዘዴ መፃፍንለማሻሻል ያለው ሚና በሠቃ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በኦሮምኛ አፈ-ፈት በሆኑ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account