dc.contributor.author | አንተነህ አየነው ዋለ | |
dc.contributor.author | ጌታቸው አንተነህ | |
dc.date.accessioned | 2021-12-30T07:46:51Z | |
dc.date.available | 2021-12-30T07:46:51Z | |
dc.date.issued | 2011-07-04 | |
dc.identifier.uri | https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/5994 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናት በርዕሰ አድባራት ወ ገዳማት መርጡለ ማሪያም ገዳም ጋር ተያይዘው የሚነገሩ ተረኮችን ይዘት እና ማህበራዊ ፋይዳ ተንተኖ ማጥናትና ማሳየት በሚል ዋና አላማ የቀረበ ነው፡፡ ይህች ጥንታዊትና ታሪካዊት ገዳም ከተመሰረተች ከ3740 ዓመት በላይ ስለሆነ የኦሪትም የሐዲስ ኪዳኑም ስርዓት የተፈጸመባት እንደ ጊዜ ቅደም ተከተላቸው ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ በዚህ ጥናት ስምንት መረጃ አቀባዮች የተሳተፉ ሲሆን ስድስቱ ቁልፍ መረጃ አቀባዮች ናቸው፡፡ የጥናቱ ዓላማም የተሳካ ይሆን ዘንድ ጽሁፋዊ ማስረጃዎችን ከመጠቀም በተጨማሪ በቃለ መጠይቅ፣ በምልከታ፣ በቡድን ተኮር ውይይት መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ የተሰበሰቡ መረጃዎችም በማስታዎሻ፣ በምስል፣ በመቅረጸ ድምጽ እና እንደአስፈላጊነቱ በቪደዮ ካሜራ በማጠናቀር መረጃዎቹ ክግብ ለማድረስ ተችሏል፡፡ እነዚህ ተረኮች በገላጭ የምርምር ዘዴ በመጠቀም እና በተረክ ትንተና ንድፍ ሃሳብ መንደርደሪያነት ለመተንተን ተሞክሯል፡፡ እንዲሁም የተጠኝ አካባቢና የማህበረሰቡ ዳራዊ ገለጻ ተቃኝቷል፡፡ በጥናቱ ሃያ ስድስት የሚሆኑ ተረኮች የተሰበሰቡ ሲሆን ከይዘታቸው አንጻር የገዳሟን ጥንታዊነት የሚዘክሩ፣ የቃል ኪዳን፣ የገዳሟን ቅድስናና ክብር ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ የፈውስ፣ የገቢራተ ተዓምራት፣ ትንቢት ነክ፣ የራዕይ እና ሉዓላዊነትን የሚያስጠብቁ ተረኮች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ | en_US |
dc.language.iso | en_US | en_US |
dc.title | በርዕሰ አድባራት ወ ገዳማት መርጡለ ማርያም ገዳም የሚነገሩ ተረኮች ይዘት ትንተና ጥናት | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |