Jimma University Open access Institutional Repository

በተማሪዎች ድርሰት ላይ የመምህራን ፅሁፋዊ ምጋቤ ምላሽ ያለው አስተዋፅኦ ትንተና በ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

Show simple item record

dc.contributor.author እጅጋየሁ በቀለ
dc.contributor.author ጥበቡ ሽቴ
dc.date.accessioned 2021-12-30T07:57:04Z
dc.date.available 2021-12-30T07:57:04Z
dc.date.issued 2011-08-05
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/5997
dc.description.abstract የዚህ ጥናት አላማ ተማሪዎች ለሚፅፏቸው ድርሰቶች መምህራን የሚሰጧቸው ፅሁፋዊ ምጋቤ ምላሽ የመፃፍ ችሎታቸውን በማሻሻል ረገድ ያለውን አስተዋጽኦ መፈተሸ ነው፡፡የአጠናን ዘዴውም መጠናዊ (Quanitative Method) ላይ የተመሰረተ ሆኖ ከፊል ሙከራዊ ነው፡፡ተጠኝዎቹ በሰሜን ሸዋ ዞን በመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ትምሀርት ቤት በ 2011ዓ.ም ትምህርታቸውን በመከታተልላይ ያሉ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ሙከራው የተካሄደው ደግሞ በተራ የእጣ ናሙና የተመረጡ ሁለት ክፍሎች እያንዳንዳቸው 41 ተማሪዎችን የያዙ አጠቃላይ 82 ተማሪዎች ናቸው፡፡ እንደኛው 9ኛA የሙከራ ቡድን ሌላው 9ኛB የጥብቅ ቡድን ተብለው ተመድበዋል፡፡ ለጥናቱ መረጃ የተሰበሰበባቸው የተማሪዎች የድርሰት መፃፍ ፈተና፣ የፅሁፍ መጠይቅና ቃለ መጠይቅ ሲሆኑ የተማሪዎች የድርሰት መፃፍ ፈተና ቅድመ ድርሰት መፃፍ ፈተና እና ድህረ ድርሰት መፃፍ ፈተና በመምህራን ታርመው በፅሁፋ ዙሪያ በሚነሱ የተለያዩ ሀሣቦች አንፃር ተተንትነዋል፡፡ ቅድመ ድርሰት መጻፍ ፈተና በሙከራ ቡድንና በጥብቅ ቡድን የተገኘውም አመካይ ውጤት በቁጥርና በመቶኛ እንዲሁም በመደበኛ ልይይት በቲ-ቴስት ‘’Independent Sample t-test’’ተሰልቶ ልዩነት አለመኖሩ ተረጋግጧል፡፡ በድህረ ድርሰት መጻፍ ፈተና ደግሞ በሙከራ ቡድን በመደበኛ ልይይት ‘’Repeated Measures Sampl t-test’’ ተሰልቶ የተገኘው ውጤትም ልዩነት መኖሩ እናበመምህራን ምጋቤ ምላሽ ማግኘት ምክንያት የመጻፍ ችሎታቸው መሻሻሉ ተረጋግጧል፡፡ ከምጋቤ ምላሽ በኋላ በድህረ ድርሰት ፈተና ጥብቅ ቡድኑ ልዩነት ባለመኖሩ መሻሻል አለመኖሩ ስሌቱ አመልክቷል፡፡ አጠቃላይ ጽሑፋዊ ምጋቤ ምላሽ የተማሪዎችን ድርሰት የመፃፍ ችሎታ በማዳበር በኩል ያለውን አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንዲሆን ያደርጉት አወንታዊ ምጋቤ ምላሽ መስጠት፤ በርካታ ምጋቤ ምላሽ በአንደ ጊዜ አለመስጠት በዋንኛነት እንደሚጠቀሱ ተረጋግጧል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title በተማሪዎች ድርሰት ላይ የመምህራን ፅሁፋዊ ምጋቤ ምላሽ ያለው አስተዋፅኦ ትንተና በ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት) en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account