Jimma University Open access Institutional Repository

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከ1922-1983 ዓ.ም. ድረስ የተፃፉ የስራ ደብዳቤዎች ቋንቋ አጠቃቀም ይዘትትንተና፡፡

Show simple item record

dc.contributor.author ቅድስት ጫንያለው
dc.contributor.author ጌታቸው አንተነህ
dc.contributor.author ለማ ንጋቱ
dc.date.accessioned 2021-12-30T08:14:47Z
dc.date.available 2021-12-30T08:14:47Z
dc.date.issued 2010-07-04
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/6003
dc.description.abstract የዚህ ጥናት አላማ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከ1922-1983 ዓ.ም. ድረስ የተፃፉ መደበኛ ደብዳቤዎችን በጥልቅ ዲስኩር ትንተና መርህ መሰረት የቋንቋ አጠቃቀም በመተንተን በተፃፉበት ዘመን የነበረውን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ምን እንደሚመስሉ ማሳየት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጥናቱ አይነታዊ የምርምር አይነት በመሆኑ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እና በደርግ ዘመን የተፃፉ የስራ ደብዳቤዎችን ለመተንተን ተሞክሯል፡፡ በጥናቱ ወቅት ደብዳቤዎቹ ከተፃፉበት ዘመን አኳያ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎችን መሠረት አድርገው ከመተንተናቸው ባለፈ ደብዳቤዎቹ ከዘመን ዘመን አኳያ ያሳዩዋቸው ልዩነቶችም ተጠቅሰዋል፡፡ ጥናቱን ለማድረግ በመሠረታዊነት ጥናቱ በተመሰረተበት ጊዜ እና ቦታ ወሰን ያሉ ሰነዶችን በመረጃ ምንጭነት ለመጠቀም ተችሏል፡፡ በዚህ መሠረት የትንተናው ውጤት እንደሚያሳየው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተፃፉ የስ ራደብዳቤዎች ከተፃፉበት ዘመን መንፈስ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ ሁኔታ አንፃር ሲተነተኑ ፖለቲካውና ሀይማኖቱ የነበራቸውን ቁርኝት፣ ፖለቲካውና የፖለቲካ አመራሩ በማህበረሰቡ ላይ ያደርስ የነበረውን አወንታዊና አሉታዊ ጫና ያሳያል፡፡ በተጨማሪ በአብዛኛው በጃንሆይ ዘመን፣ በአንፃራዊነት በደርግ ዘመን የተፃፉ ደብዳቤዎች ከቃላትአጠቃቀም አንፃር አሁን ካለንበት ዘመን ለየት ያሉ ቃላት ይጠቀሙ እንደነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡ በሌላ በኩል ደብዳቤዎቹ ከተፃፉበት የዘመን መንፈስ አንፃር ሲተነተኑ የፖለቲካ አመራሩ ግብርንና መሰል ጉዳዮችን መሠረት በማድረግ በዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍል ላይ ኢኮኖሚያዊ ጫና ያደርሱ እንደነበ መረዳት ተችሏል፡፡ በጃንሆይ ዘመን የተፃፉ ደብዳቤዎች ለንጉሰ ነገስቱ፣ ለንጉሰ ነገስቱ ሹማምንት እና ለላይኛው ለፖለቲካና የኢኮኖሚ መደብ የአዋቂነት፣ የልበ ብርሃንነት፣ የጌትነት፣ የጀግንነት፣ የአስተዋይነት፣ የችግር ፈችነት፣የደግነት ወዘተ ውክልና እና ሙገሳ ሲሰጡ በአንፃሩ ለታችኛው መደብ ደግሞ የምፅዋት ጠባቂነት፣ የአጥፊነት፣ ያላዋቂነት፣ የስልጣን ውስንነት እና የመሳሰሉት ውክልና ተሰጥቶት እናያለን፡፡ በደርጉ ዘመን የተፃፉ ደብዳቤዎች በአንፃሩ ከግለሰብ ይልቅ አብዮታዊት ኢትዮጵያን፣ ህብረተሰባዊት ኢትዮጵያን፣ ዘመቻን እና ወዘተ ሲያወድሱ ይስተዋላል፡፡ በተጨማሪም የፊውዳሉን ስርዓት ኮናኝ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ በአጠቃላይ በቀድ en_US
dc.language.iso other en_US
dc.title በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከ1922-1983 ዓ.ም. ድረስ የተፃፉ የስራ ደብዳቤዎች ቋንቋ አጠቃቀም ይዘትትንተና፡፡ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account