Jimma University Open access Institutional Repository

ከ1966 - 2010 ዓ.ም የተቃዉሞ ቃል ግጥሞች ማህበረሰባዊ አንድምታ ትንተና በላይ ጋይንት ወረዳ

Show simple item record

dc.contributor.author ዉዴ ጌትነት
dc.contributor.author ለማ ንጋቱ
dc.date.accessioned 2021-12-30T08:20:29Z
dc.date.available 2021-12-30T08:20:29Z
dc.date.issued 2011-08-06
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/6005
dc.description.abstract ይህ ጥናት በላይ ጋይንት ወረዳ የተቃዉሞ ቃል ግጥም ማህበራዊ ፋይዳ እና አንድምታ ማሳየት በሚል ዋና ዓላማ የቀረበ ነው። ጥናቱ የተሳካ ይሆን ዘንድ ጽሁፋዊ ማስረጃዎችን ከመጠቀም በተጨማሪ በቃለ መጠይቅ፣ በምልከታ፣ በቡድን ተኮር ውይይት መረጃዎች ተሰብስበዋል። የተሰበሰቡ መረጃዎችም በማስታዎሻ፣ በምስል፣ በመቅረጸ ድምጽ እና እንደአስፈላጊነቱ በቪዲዮ ካሜራ በማጠናቀር መረጃዎቹን መሰብሰብ ተችሏል። እነዚህ የተቃዉሞ ቃል ግጥሞች ገላጭ የምርምር ዘዴ በመጠቀም መረጃዎች ተተንትነዋል። እንዲሁም የተጠኝ አካባቢና የማህበረሰቡ ዳራዊ ገለጻ ተቃኝቷል። በመሆኑም የተሰበሰቡትን የተቃዉሞ ቃል ግጥሞች ከይዘታቸው አንጻር አስተዳደራዊ ችግሮችን፣ የመሬት ኢ-ፍትሃዊ ክፍፍል፣ አድሎአዊነትን የሚጠቁሙ ሆነዉ ተገኝተዋል። ከፖለቲካ ልዩነቶች አንጻር ማህበረሰቡ የሚጠላዉንና የሚወደዉን አመላካች ሃሳቦች የተንጸባረቁባቸዉ ሆነዉ ተገኝተዋል። ስለዚህ የዚህን ጥናት ዉጤት መሰረት በማድረግ የአካባቢዉን ማህበረሰብ ለመለወጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የተቃዉሞ ቃል ግጥሞቹን በመረጃነት መጠቀም ቢቻል ጥሩ ነዉ። en_US
dc.title ከ1966 - 2010 ዓ.ም የተቃዉሞ ቃል ግጥሞች ማህበረሰባዊ አንድምታ ትንተና በላይ ጋይንት ወረዳ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account