dc.contributor.author | በይታይሽ ዴሲሳ | |
dc.contributor.author | ምህረት ሳዳሞ | |
dc.contributor.author | ይክበር ይመስገን | |
dc.date.accessioned | 2022-01-10T09:44:22Z | |
dc.date.available | 2022-01-10T09:44:22Z | |
dc.date.issued | 2021-01-06 | |
dc.identifier.uri | https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/6037 | |
dc.description.abstract | የዚህ ጥናት ዋና አላማ የማንበብ ብልሀቶችን ነጥሎ ማስተማር የተማሪዎችን አንብቦ የመረዳት ችሎታ ለማዳበር ያለውን ሚና መመርመር ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄው በኦሮሚያ ክልል በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በሀረቶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አማርኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ በሚማሩ የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ የጥናቱ መረጃ በፈተናና በጽሁፍ መጠይቅ ተሰብስቧል፡፡መረጃው ከፊል ፍትነታዊ የምርምር ስልትን በመከተሉ የተገኘውን ውጤት ለመተንተን ገላጭ ስታትስቲክስና ድምዳሜያዊ ስታትስቲክ ስራ ላይ ውሏል፡፡የሙከራና የቁጥጥር ቡድን ከልምምድ በፊት ተመሳሳይ ፈተና ተሰጥቷቸው ውጤቱ በቲ-ቴስት ሲሰላ የቲ-ቴስቱ ዋጋ0.015 ስለሆነ በሁለቱ መካከል የአንብቦ መረዳት ችሎታ መበላለጥ እንደለላቸው ተረጋግጦ ወደ ጥናቱ ተገብቷል፡፡ በዚህም መሰረት ለሙከራ ቡድኑ በብልሀቶቹ ስልጠና በመስጠት እና ቅድመ ስልጠና የጽሁፍ መጠይቅ እንዲሞሉ በማድረግ ትምህርቱን እንዲከታተሉ ሲደረግ የቁጥጥር ቡድኑ ደግሞ በተለመደው የአንብቦ መረዳት ማስተማሪያ ዘዴ እንዲማሩ ተደርጓል፡፡የማንበብ ብልሀቶች አንብቦ መረዳትን ለማሻሻል ያላቸው አስተዋጽዖ ምን እንደሚመስል በጥንድ ቲ-ቴስት የተሰላ ሲሆን፣ በቅድመ ልምምድ የሙከራ ቡድን የአንብቦ መረዳት ውጤት አማካይ =11.71 ፣ መደበኛ ልይይት =4.00 እንዲሁም በድህረ ልምምድ አማካይ=17.76፣ መደበኛ ልይይት =3.39 ስያሳይ የቲ-ስሌት ዋጋ (19.06)፣ P<.05፣ ባለ ሁለት ጫፍ በመሆኑ ጉልህ ልዩነት አሳይቷል፡፡የብልሀት አጠቃቀም ደረጃቸውን በተመለከተ ደግሞ ነጻ ቲ-ቴስት ተግባራዊ ሆኗል፤ ውጤቱም ከስልጠና በኋላ ብልሀቶቹን በከፍተኛ ደረጃ መጠቀም ችለዋል፡፡በመጨረሻም የጥናቱን ውጤት ያሳየው የማንበብ ብልሃቶችን ነጥለው ማሰልጠን የተማሪዎችን የብልሃት ግንዛቤና አጠቃቀም በማሳደግ የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ለማሳደግ ከተለመደው ማስተማሪያ ዘዴ በተሻለ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ነው፤ ውጤቱንም መሰረት በማድረግ የተጠቆሙት አስተያየቶች፤-ይህ ጥናት በአንድ ትምህርት ቤት ብቻ የተከናወነ በመሆኑ ሁሉንም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስለማይወክል በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ዙርያ ተጨማሪና ተመሳሳይ ጥናቶች ቢደረጉ፣የማንበብ ብልሀት ስልጠናም በአንድ ጀንበር የሚጠናቀቅ ጉዳይ ባለመሆኑ መምህራንም ሆኑ ተማሪዎች ስለ ብልሀቶቹ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸውናበመማሪያ ክፍል ውስጥ መጠቀም እንዲችሉ ጉዳዩ የሚመለከታየቋንቋ ባለሞያዎች መማሪያ መጻሕፍቱን ሲያሻሽሉ ብልሀቶቹን ለማካተት ቢሞክሩ የሚሉ ናቸው፡፡ | en_US |
dc.language.iso | en_US | en_US |
dc.title | የማንበብ “ብልሀቶችን ነጥሎ ማስተማር አንብቦ የመረዳት ችሎታን ችሎታን ለማጎልበት ያለው ሚና (በኦሮሚያ ክልል ሀረቶ ሁለተኛ ደረጃ፣ አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት በሚማሩ የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት) | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |