Jimma University Open access Institutional Repository

በኦሮሚያ ክልል የተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያ መፃህፍት ለህብረ-ባህላዊነትና ብዝሃነት የሰጡት ትኩረት ፍተሻ (በ7ኛና በ8ኛ ክፍል ተተኳሪነት)

Show simple item record

dc.contributor.author ጌቱ ጫካ ጉሉማ
dc.contributor.author ምህረት ሰዳሞ
dc.contributor.author ማንያለው አባተ
dc.date.accessioned 2022-01-10T13:46:06Z
dc.date.available 2022-01-10T13:46:06Z
dc.date.issued 2021-06-06
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/6044
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ አዘጋጅነት አማርኛን እንደሁለተኛ ቋንቋ ለ7ኛና ለ8ኛ ክፍል በ2009 ዓ/ም የተዘጋጁት ማስተማሪያ መፃህፍት ለህብረ-ባህላዊነትና ብዝሃነት የሰጡትን ትኩረት መፈተሽ ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በመማሪያ መፅሃፍቱ ለህብረ-ባህላዊነትና ብዝሃነት የሰጡትን ትኩረት ለመለየት የህብረ-ባህላዊነትና ብዝሃነት መገለጫ ከሆኑት ከባህል፣ ከኃይማኖትና ከፆታ አኳያ በመማሪያ መጽሃፍቱ ግብዓት የሆኑት የምንባቦች፣ የመመሪያዎችና የመልመጃዎች አቀራረብ የተሰጠው ትኩረት ምን እንደሚመስል መፈተሽ ነው፡፡ ጥናቱ የተከተለው ዓይነታዊ የምርምር ስልትን ሲሆን በዋናነት ጥቅም ላይ የዋለው የሰነድ ፍተሻ ነው፡፡ ከሰነድ ፍተሻው የተሰበሰቡት መረጃዎች በገላጭ ስታስቲካዊ ዘዴን በመከተል በጥናቱ ውስጥ ከተነሱት መሪ ጥያቄች አኳያ የጥናቱን ዓላማ መሰረት በማድረግ ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ውጤትም እንደሚያሳየው በሁለቱም መማሪያ መጽሃፍት ለህብረ-ባህላዊነትና ብዝሃነት መገለጫ ለሆኑት ለባህል፣ ለሃይማኖትና ለፆታ እኩል ትኩረት አልተሰጠም፡፡ ከባህል አኳያ በመማሪያ መፃህፍቱ ከቀረቡት 55 ምንባቦች ውስጥ 7(12.73 በመቶ) ባህልን ያልጠበቁ ሆኖ ተገኝተዋል፡፡ ከሃይማኖት አኳያ ሲታይ አንድ ምንባብና አንድ ምሳሌያዊ አነጋገር የክርስትና ሃይማኖትን ያንጸባረቁ ስለሆነ ተማሪዎቹ የተለያየ ኃይማኖት ተከታይ ሊኖሩ ስለሚችል መታየት እንዳለባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከፆታ አኳያ የተገኘው ውጤት እንደሚያስረዳው በመማሪያ መፃህፍቱ ቋንቋውን ሊያዳብሩ ይችላሉ ተብለው የቀረቡት ምንባቦች፣ መመሪያዎችና መልመጃዎች ውስጥ በግብዓትነት የቀረቡት ስሞች፣ ግለ-ታሪኮች፣ ግሶች፣ ሀረጎችና ዐረፍተ ነገሮችን በተደረገው ፍተሻ የተገኘው አማካይ ውጤት 20.03 በመቶኛ የወንድ ፆታ አመልካች ስሞች፣ ግሶች፣ ሀረጎችና ዐረፍተ ነገሮች ከሴት ፆታ ብልጫ እንዳላቸው ለማየት ተችሏል፡፡ ከዚህ የምንረዳው የፆታ እኩልትን ያልጠበቀ ሆኖ መገኘቱን ነው፡፡ በመሆኑም በሁለቱም መማሪያ መፃህፍት ዝግጅት ወቅት የማስተማሪያ ግብዓት የምንባቦች፣ መመሪያዎችና መልመጃዎች አቀራረብ ከህብረ-ባህላዊነትና ብዝሃነት አኳያ በመለየት ማሻሻያ ቢደረግ የተሻለ ነው የሚል ጥቆማ ለመስጠት አጥኚው ይወዳል፡ en_US
dc.language.iso other en_US
dc.title በኦሮሚያ ክልል የተዘጋጁት የአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያ መፃህፍት ለህብረ-ባህላዊነትና ብዝሃነት የሰጡት ትኩረት ፍተሻ (በ7ኛና በ8ኛ ክፍል ተተኳሪነት) en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account