Jimma University Open access Institutional Repository

በደብረ ማርቆስ ከተማ በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች የመጻፍ ክሂል ችሎታ ንጽጽር በ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author ቦጋለ ስብሃቱ
dc.contributor.author ጥበቡ ሽቴ
dc.date.accessioned 2022-02-16T07:18:10Z
dc.date.available 2022-02-16T07:18:10Z
dc.date.issued 2013
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/6289
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ በመንግስትና በግል ት/ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎችን የመፃፍ ክሂል ችሎታ ፈትሾ ማነፃፀር ነው፡፡ ይህን አለማ ከግብ ለማድረስ አነፃፃሪ ንድፍ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ በአላማ ተኮር የንሞና ዘዴ ከመንግሰት ት/ቤቶች የጎዛምን አጠ/ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከግል ት/ቤት ደግሞ ሆህያት አካዳሚ ተመርጠዋል፡፡ በመንግስት ት/ቤቶች ካሉት ስምንት የመማሪያ ክፍሎች ጠቅላላ የጣ ንሞና ዘዴ ወረቀት ጠቅልሎ እጣ በማውጣት ተመርጠዋል፡፡ የግል ት/ቤቶች ካሉት ሁለት የመማሪያ ክፍሎች 40 ተማሪዎች በአጠቃላይ ናሙና ዘዴ ተመርጠዋል፡፡ የመፃፍ ክሂል ችሎታ ፈተና ከጥናቱ ተሳታፊዎች መረጃ ለመሰብሰብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ የተሰበሰበውን መረጃ በአግባቡ ከተደራጀ በኋላ ነጠላ ናሙና ቲ-ቴስትና በነፃ ናሙና ቲ-ቴስት የመረጃ መተንተኛ ሰልት ተተንትኗል፡፡ በትናትናው መሰረትም በነጠላ ናሙና ቴስት የመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች የመፃፍ ክሂል ችሎታ ፈተና በአማካኝ ውጤቱ ያለው ልዩነት የጉልህነት ደረጃ (t(39)=3.1981፤p<0.003) ሲሆን ከመቶ ተማሪዎች የመፃፍ ክሂል ችሎታ አማካኝ ውጤት በሚጠበቀው መካከል ጉልህ ልዩንት መኖሩን ያመለክታል፡፡ የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች የመፃፍ ክሂል ችሎታ ፈተና በአማካኝ ያለው የጉልህነት ልዩንት ደረጃ (t(39)= 2.655, p=0.0011) ሲሆን ከመቁረጫ ነጠብ (p>0.05)በልጦ ተገኝቷል፡፡ ይህም በግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች የመፃፍ ክሂል ችሎታ አማካኝ ውጤትና በሚጠበቀው አማካኝ ውጤት መካከል ጉልህ ልዩንት አለመኖሩን ያመለክታል፡፡ በመንግስት ት/ቤትና በግል ት/ቤት ተማሪዎች የመፃፍ ክሂል ችሎታ ፈተና ውጤት አማካኝ መካከል ያለውን ልዩንት ጉልህ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ መረጃው በነፃ ናሙና ቲ-ቴስት ተሰልቶ ውጤቱ (t(78)= 4.085 p<0.0001 ከመቁረጫ ነጥቡP=0.01) አንሶ ተገኝቷል፡፡ በጉልህነት የጥንቃቄ ደረጃ ተሰልቶ (ª=1%) ሆኖ ስለተገኘ መካከለኛ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ከዚህም በመነሳት የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች የመፃፍ ክሂል ችሎታ የተሸለ ደረጃ ላይ እንዳለ ተረጋግጧል፡፡ የህን መደምደሚያ መሰረት በማድረግም የልዩነት ምክንያትምን እንደሆነ በቀጣይ ጥናት ቢካሄድበት የሚል ጥቆማ ቀርቧል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title በደብረ ማርቆስ ከተማ በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች የመጻፍ ክሂል ችሎታ ንጽጽር በ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account