Jimma University Open access Institutional Repository

የመምህራን የአንብቦ መረዳት ብልሀቶች የክፍል ውስጥ አተገባበር በደቡብ ወሎ የተንታና መቅደላ ወረዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በ9ኛ እና በ10ኛ ክፍል መምህራን ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author አስማረ ዳምጠው አመኑ
dc.contributor.author ለማ ንጋቱ
dc.contributor.author ኤባ ቴሬሳ
dc.date.accessioned 2022-02-16T07:44:07Z
dc.date.available 2022-02-16T07:44:07Z
dc.date.issued 2013
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/6295
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ በደቡብ ወሎ የተንታና መቅደላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛ እና የ1ዐኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መምህራን በክፍል ውስጥ የሚከተሏቸውን የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች መመርመር ነው፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በደቡብ ወሎ የተንታና መቅደላ ወረዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ9ኛ ና 1ዐኛ ክፍል መምህራን የሆኑትን 31 መምህራን የአስፋወሰን ፣ የአጅባር ፣ የደበቅ ፣ የወርጠጀና የመቅደላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ናቸው፡፡ በጥናቱ ውስጥ ለመረጃ መሰብሰቢያነት በሥራ ላይ የዋሉት መሳሪያዎች ምልከታና ቃለ መጠይቅ ናቸው፡፡ የጥናቱ ዋነኛ የመረጃ ማሰብሰቢያ መሳሪያ ምልከታ ሲሆን የአንብቦ መረዳት ብልሃቶች አተገባበር ደረጃዎችን በተመለከተ ለቅድመ ንባብ ፣ ለሂደታዊ ንባብ /ጊዜ ንባብ/ እና ድህረ ንባብ አተገባበርን ምልከታ የሚረዱ ቸክሊስት በማዘጋጀት 31ዱም ተጠኝ መምህራን ለእያንዳንዳቸው ሁለት ክ/ጊዜ በድምሩ 62 ክፍለ ጊዜ የሸፈነ ምልከታዎች ተከናውነው መረጃው በአይነታዊ ዘዴ በመቸኛ ተሰልቶ ተከናውኗል፡፡ የምልከታ መረጃውን መሠረት በማድረግ የተሰበሰበውን መረጃ ለማጠናከረና መምህራን በአተገባበሩ ሂደት ያላቸውን ተሳትፏዊ ግንዛቤ ያለበትን ሁኔታ በማሳየት የሚያስችሉ በ3ቱም የአተገባበር ደረጃዎች ላይ የተመረኮዙ ከ2ዐ በላይ የቃለ መጠይቅ ጥያቄዎች ተዘጋጅተው በምልከታ ጊዜ በታዩ የአተገባበር ሁኔታ አመላካች የሆኑ ዝቅተኛ አተገባበር ላይ የሚገኙ 6 መምህራን በአላቸው ደረጃ ተለይተው ከአጠቃላዩ የተጠኝ ናሙናዎች የተመጣጠነ ውክልና ባላቸው የመምህራን ቁጥር ላይ መረጃ የተሰበሰበ ሲሆን በዚህም ተጽእኖ ሊያደርሱ የሚችሉ ተለወጦዎች የሚያሳዩትን ሁኔታ ማየት ተችሏል፡፡ በምልከታና ቃለ መጠይቁ የመምህራኑ የአተገባበር ደረጃ የተለያየ ቢሆንም በ3ቱም የአተገባበር ደረጃዎች ማለት በቅድመንባብ ፣ በጊዜ/ሂደታዊ/ንባብና ድህረ ንባብ የአተገባበር ብልሃቶች የመምህራን የክፍል ውስጥ አተገባበር ያለበት ደረጃ በአማካይ በቅድመ ንባብ ጊዜ ዝቅተኛና መረጃ ያልተተገበሩ 74.8 ሲሆኑ 25.2 ከፍተኛና መካከለኛ ሆኖ የመምህራን አተገባበር ደረጃ ዝቅብሎ ታይቷል፡፡ በጊዜ ንባብ /ሂደታዊ ንባብ ደግሞ 77. ዝቅተኛና ጭራሽ ያልተተገበረ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህም ሂደታዊ ንባብ በአተገባበር የአንብቦ መረዳት ብልሃት ያልተሳካ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ የቀጣዩ የድህረ ንባብ የመምህራን አተገባበር በተነፃፃሪነት ሲታይ ከሁለቱ ሻል ያለ ነገር ግን ከችግር ውስጥ ያለ መሆኑ በአማካይ 6ዐ.ዐ6 ዝቅተኛና ጭረሻ ያልተተገበረ ተግባር ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመምህራን የአንብቦ መረዳት አተገባበር ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ተለወጠዎች /ሁኔታዎች/ በጥቅም ላይ ከዋሉት ምልከታና ቃለ መጠይቅ በተገኘው መረጃ መሠረት ተከታታይነት የለው የመምህራን ሙያዊ የሥራ ላይ ሥልጠና አለማግኘት ፣ የመምህራን የርስ በርስ ልምድ ልውውጥ የተነሳሽነት ማነስ ጎልተው የታዩ ችግሮች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ይህንኑ መሠረት በማድረግ ጥናቱ ለወደፊቱ ይጠቅማሉ የሚል በችግሮቹ መፍቻ የመፍትሄ ገሳቦች ጠቁሟል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title የመምህራን የአንብቦ መረዳት ብልሀቶች የክፍል ውስጥ አተገባበር በደቡብ ወሎ የተንታና መቅደላ ወረዳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በ9ኛ እና በ10ኛ ክፍል መምህራን ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account