dc.contributor.author | ስመኝ አየለ | |
dc.contributor.author | ጥበቡ ሽቴ | |
dc.date.accessioned | 2022-02-17T11:27:39Z | |
dc.date.available | 2022-02-17T11:27:39Z | |
dc.date.issued | 2014 | |
dc.identifier.uri | https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/6354 | |
dc.description.abstract | የተከታታይ ምዘናን መጠቀም የመማር ማስተማር ሂደትን ውጤታማ እንደሚያደርግ ይታመናል። በመሆኑም ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ተከታታይ ምዘና አተገባበር ሂደት ፍተሻ ላይ ያተኮረ ነው። የጥናቱ ዋና ዓላማ በ1ኛ ደረጃ ከ5ኛ-8ኛ ክፍል በመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የተከታታይ ምዘና አተገባበር ሂደት ምን እንደሚመስል መፈተሽ ነው። ጥናቱ ገላጭ የዳሰሳ ዘዴን (Descriptive Survay Method) የተከተለ ሲሆን መምህራንና ተማሪዎች መረጃ በመሰጠት በጥናቱ ተካተዋል። መረጃ ለመሰብሰብ ምልከታ፣ የጽሁፍ መጠይቅ፣ ቃለ መጠይቅ እና ሰነድ ፍተሻ ጥቅም ላይ ውለዋል። መረጃዎቹም በመጠናዊና በአይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ዘዴ ተተንትነው በመቶኛ፣ በሰንጠረዥና በገለጻ ቀርበዋል። የጥናቱ ውጤት የሚያሳየው የተከታታይ ምዘና ስልቶችን አብዛኛው መምህራን (75.6%) ሁልጊዜ፤ ጥቂቶቹ (9.6%) ደግሞ አልፎ አልፎ እንድሚተገብሩ ነው። በሌላ በኩል አብዛኞቹ ተማሪዎች (75.05%) መምህራኑ የተከታታይ ምዘና ስልቶችን በስራ ላይ የሚያውሉት አልፎ አልፎ እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፤ የተቀሩት (24.48%) ደግሞ ሁልጊዜ እንደሚተገብሩት ገልጿል። በአጠቃላይ የጥናቱ ውጤት የሚያመለክተው የተከታታይ ምዘና ስልቶች ሙሉ በሙሉ እየተተገበሩ ነው ለማለት አያአስደፍርም። የጅማ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የተከታታይ ምዘናን አተገባበር ውጤታማ ለማድረግ ለመምህራን ተከታታይ ስልጠና መስጠት፣ በቂ የክፍለ ጊዜ ድልደላ ማድረግ፣ አስፈላጊውን የትምህርት መርጃ መሳሪያ ማሟላት እና የተከታታይ ምዘናው በዕቅድ እንዲመራ በማድረግ ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚያስችል የመፍትሄ ሃሳብ ተሰጥቷል። | en_US |
dc.language.iso | en_US | en_US |
dc.title | የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የተከታታይ ምዘና አተገባበር ዳሰሳ በጅማ ከተማ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ከ5ኛ-8ኛ ክፍል ተተኳሪነት | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |