Jimma University Open access Institutional Repository

የኢትዮጵያ ቋንቋ (ዎች) እና ስነ-ጽሁፍ አማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ድህረ ምረቃ መርሀ ግብር

Show simple item record

dc.contributor.author ጎዴ ምንውዬ
dc.contributor.author ጥበቡ ሽቴ
dc.contributor.author ይክበር ይመስገን
dc.date.accessioned 2022-02-18T12:04:26Z
dc.date.available 2022-02-18T12:04:26Z
dc.date.issued 2014
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/6361
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ የተማሪዎች የማዳመጥ ብልሀት አጠቃቀም ከአዳምጦ መረዳት ችሎታቸው ጋር ያለውን ተዛምዶ መመርመር ነበር፡፡ ጥናቱ ተዛምዷዊ ንድፍን የተከተለ ሲሆን ስታስቲካዊ ገላጭ የምርምር ስልትን ተከትሎ የቀረበ ነው፡፡ የጥናቱን ተሳታፊዎች ለመምረጥም እድል ሰጭ ናሙናን መሰረት በማድረግ በረድፋዊ ንሞናን በመጠቀም ተመርጠዋል፡፡ ተሳታፊዎቹም በሙጃ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ 2013 ዓ.ም በአስርኛ ክፍል የሚማሩ 154 ተማሪዎች ናቸው፡፡ መረጃውም የማዳመጥ ብልሀት መለኪያ በፅሁፍ መጠይቅና በአዳምጦ መረዳት የችሎታ መለኪያ ፈተና ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎቹም መጠናዊ የምርምር ዘዴን በመጠቀም በ(SPSS 20) ኮምፒውተር ሶፍት ዌር በፒርሰን የተዛምዶ ተሰልተው በገላጭና ድምዳሜያዊ ስታትስቲክስ ተተንትነዋል፡፡ በፅሁፍ መጠይቅ በተሰበሰበው መረጃ መሰረት የተማሪዎች የብልሃት አጠቃቀም በጥቅል የብልሃት አይነት 75 (50%) አብዛኛውን ጊዜ የሚጠቀሙና ሁልጊዜ የሚጠቀሙ ሆነው ሲመዘገቡ 41 (27.33%) ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ የማይጠቀሙና በጭራሽ የማይጠቀሙ ሆነው ተመዝግበዋል፡፡ ከብልሃት አይነቶች መካከል የበለጠ የሚጠቀሙት አእምሯዊ ብልሃት ሲሆን ይህም በፅሁፍ መጠይቅ በተገኘው መረጃመሰረት ከፍተኛ ተጠቃሚ (M= 3.85, SD=1.15) በሆነ ውጤት ከሁለቱ የብልሃት አይነት ቀዳሚ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በማዳመጥ ብልሃት አጠቃቀምና በአዳምጦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በተመለከተ አጠቃላይ (r=.523) ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በመሆኑም በተማሪዎች በማዳመጥ ብልሃት አጠቃቀምና በአዳምጦ መረዳት መካከል አዎንታዊና ጉልህ የሆነ ተዛምዶ እንዳለው በስታትስቲክስ ጉልህ ልዩነት (p<0.05) ታይቷል፡፡ ስለዚህ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የማዳመጥ ብልሃትን መጠቀም አዳምጦ የመረዳት ችሎታን ለማጎልበት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በመገንዘብ ማዳመጥን በክፍል ውስጥ በሚያስተምሩበት ጊዜ ተማሪዎች ብልሃትን እንዲጠቀሙ ቢደረግ፣ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ማዳመጥን በሚያስተምሩበት ጊዜ የተማሪዎችን የብልሃት አጠቃቀም ያማከለ ቢሆን፣ የመማሪያ መጽሐፍት በተለይም ደግሞ በማዳመጥ ተግባር ላይ ያሉ መመሪያዎችና ትዕዛዛት የማዳመጥ ብልሃትን የሚያስጠቅሙ ሆነው ቢዘጋጁ የሚሉ ለተማሪዎች አዳምጦ የመረዳት ችሎታ እድገት ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በመሆኑ በቀጣይ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ተጨማሪና ሰፊ ጥናት ቢካሄድ የተሻለ ግንዛቤ ሊገኝ ይችላል፡፡ የሚሉ የመፍትሄ ሀሳቦች ተጠቁመዋል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title የኢትዮጵያ ቋንቋ (ዎች) እና ስነ-ጽሁፍ አማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል ድህረ ምረቃ መርሀ ግብር en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account