Jimma University Open access Institutional Repository

የኦሮመኛ አፈ-ፈት ተማሪዎች በአማርኛ ጽሑፍ ላይ የሚፈፅሟቸው ስህተቶች እና የስህተት ምንጭ ትንተና፤ (በጮራ ቦተር ወረዳ ሦስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

Show simple item record

dc.contributor.author ቱሉ ንጉሱ
dc.contributor.author ማንያለው አባተ
dc.contributor.author ጥበቡ ሽቴ
dc.date.accessioned 2022-02-22T08:28:05Z
dc.date.available 2022-02-22T08:28:05Z
dc.date.issued 2014
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/6401
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ኦሮመኛ አፈ-ፈት ተማሪዎች በአማርኛ ጽሑፍ ላይ የሚፈጽሟቸውን ስህተቶችና የስህተት ምንጮችን መመርመር ነው፡፡ ተጠኚ ተማሪዎቹ በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን በጮራ ቦተር ወረዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የዘጠነኛ ክፍል ኦሮመኛ አፍ-ፈት ተማሪዎች ናቸው፡፡ በጥናቱ የተካተቱት 300 ተማሪዎች ሲሆኑ የተመረጡትም በቀላል የእጣ ንሞና ዘዴ ነው፡፡ ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለማግኘት በተጠኚ ተማሪዎቹ በሁለት ዙር 300 ድርሰቶች እንዲጽፉ ተደርጓል፡፡ በነዚህ ድርሰቶች መሰረት ተማሪዎቹ በጽሑፋቸው ለይ የሚፈጽሟቸውን ስህተቶች ለመለየት ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በተጠኚ ተማሪዎቹ ከተሞሉ የጽሑፍ መጠይቆች እና ከአማርኛ ቋንቋ መምህራን ቃለ መጠይቆች መረጃ ተሰብስቧል፡፡ በነዚህ መረጃዎች ለተማሪዎች ስህተት መፈጸም ምክንያት ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮችን ለመለየት ተሞክሯል፡፡ ከድርሰት እርማት በተገኘው መረጃ መሰረት ጠቅላላ የስህተቶች ብዛት 2722 ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 1341 (49.21) የቋንቋ አጠቃቀም፣ 911 (33.46%) የሥርዓተነጥብ አጠቃቀም ስህተቶች እና 470 (17.26%) የቋንቋ አወቃቀር ስህተቶች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ተማሪዎች ከጻፏቸው ድርሰቶች እንዲሁም በተማሪዎች እና በመምህራን ከተሞሉ መጠይቆች በተገኙ መረጃዎች መሰረት የስህተቶቹ ምንጮች የማስተማሪያ መሳሪያዎች ዝግጅትና የማስተማሪያ ዘዴ ድክመት እና የስነልቦናዊ ሁኔታዎች ተጽእኖ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ እነዚህን ችገሮች ለማቃለል የማስተማሪያ መሳሪየዎችን አዘገጃጀት እና የማስተማሪያ ዘዴወችን ማሻሻል፤ እንዲሁም ተማሪዎች ትምህርቱን በፍላጎት እንዲማሩ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት የሚሉ መፍትሄ ሀሳቦች ተጠቁመዋል፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title የኦሮመኛ አፈ-ፈት ተማሪዎች በአማርኛ ጽሑፍ ላይ የሚፈፅሟቸው ስህተቶች እና የስህተት ምንጭ ትንተና፤ (በጮራ ቦተር ወረዳ ሦስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት) en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account