Jimma University Open access Institutional Repository

በጪንጊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የአስረኛ ክፍል ኦሮመኛ አፍ ፈት ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ቃላዊ ተግባቦታዊ ብቃትን ለማዳበር የቡድን ሥራ አጠቃቀም ሚና ፍተሻ ሙከራዊ ጥናት

Show simple item record

dc.contributor.author ዳቦሽ ይደግ ዘዉዴ
dc.contributor.author በቃሉ ፈረደ
dc.contributor.author ጥበቡ ሽቴ
dc.date.accessioned 2022-02-24T13:12:24Z
dc.date.available 2022-02-24T13:12:24Z
dc.date.issued 2014
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/6488
dc.description.abstract የዚህ ጥናት አብይ ዓላማ በኦሮምኛ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ የአስረኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት የቡድን ሥራን በመጠቀም ቃላዊ ተግባቦትን በማስተማር የቃላዊ ተግባቦት ብቃታቸውን ለማዳበር ያለውን አስተዋጽኦ በከፊል ፍትነታዊ ምርምር መፈተሸ ነበር፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካትም በጭንጊ የሚገኘው የጭንጊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአመቺ ናሙና ተመርጧል፡፡ በትምህርት ቤቱ ከሚገኙት ስድስት የአስረኛ ክፍል የመማሪያ ክፍሎች የአንዱን ክፍል ተማሪዎች ለሁለት በመክፈል በቀላል የእጣ ናሙና ተመርጠዋል፡፡ በመሆኑም የሙከራው ቡድን ተማሪዎች በቡድን ሥራ እየታገዙ ቃላዊ ተግባቦትን ሲማሩ፣ የቁጥጥር ቡድኑ ተማሪዎች ደግሞ በተለመደው የቃላዊ ተግባቦት ትምህርት አቀራረብ የቃላዊ ተግባቦት ትምህርትን በስድስት ሳምንታት ለ12 ክፍለ ጊዜያት እንዲማሩ ተደርጓል፡፡ መረጃዎቹ በቃላዊ ተግባቦት ብቃት ፈተና በቅድመትምህርት እና በድህረትምህርት ተሰብስበዋል፡፡ በቃላዊ ተግባቦት ፈተና የተሰበሰበው መረጃ በየአይነት ከተደራጀ በኋላ በገላጭና በድምዳሜያዊ ስታትስቲክስ (የነጻ ናሙናዎች ቲ-ቴስት) ተተንትንዋል፡፡ በውጤት ትንተናው መሰረትም የሙከራው ቡድን ድህረትምህርት የቃላዊ ተግባቦት ብቃት ፈተና አማካይ ውጤት(16.63) ከቁጥጥሩ ቡድኑ የቃላዊ ተግባቦት ብቃት ፈተና አማካይ ውጤት(13.60) በልጦ ጉልህ ልዩነት (p=0.000) አሳይቷል፡፡ ከጥናቱ ግኝት በመነሳትም በቡድን ሥራ ቃላዊ ተግባቦትን ማስተማር የተማሪዎችን የቃላዊ ተግባቦት ብቃት ለማሳደግ ከተለመደው የቃላዊ ተግባቦት ማስተማሪያ ዘዴ የበለጠ አስተዋጽኦ አለው ከሚል መደምደሚያ ላይ ተደርሷል፡፡ ስለዚህም የተማሪዎችን የአማርኛ ቋንቋ ቃላዊ ተግባቦትን ለማዳበር በቃላዊ ተግባቦት የማስተማር ዘዴዎች ውስጥ ተማሪዎች እራሳቸውን ችለው መማር እንዲችሉ የቡድን ሥራን በመጠቀም በማስተማር የተማሪዎችን ቃላዊ ተግባቦት ብቃታቸውን የሚሻሻልበትን ሁኔታ ሊፈጥር ይችላል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title በጪንጊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የአስረኛ ክፍል ኦሮመኛ አፍ ፈት ተማሪዎች በአማርኛ ቋንቋ ቃላዊ ተግባቦታዊ ብቃትን ለማዳበር የቡድን ሥራ አጠቃቀም ሚና ፍተሻ ሙከራዊ ጥናት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account