Jimma University Open access Institutional Repository

በደቡብ ክልል ሥራ ላይ ባሉ የ5ኛና 6ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍት ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ግምገማ

Show simple item record

dc.contributor.author በፈለቀች እሸቱ
dc.contributor.author በቃሉ ፈረደ
dc.contributor.author ሀብታሙ እንግዳው
dc.date.accessioned 2022-02-24T13:18:11Z
dc.date.available 2022-02-24T13:18:11Z
dc.date.issued 2014
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/6489
dc.description.abstract በዚህ ጥናት በደቡብ ክልል ስራ ላይ ባሉ በ5ኛና 6ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍት ዉስጥ የተካተቱ የሰዋስዉ ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ምን እንደሚመስል ተገምግሟል፡፡የጥናቱን ዓላማ ለማሳካት ገላጭ የምርምር ንድፍ የተመረጠ ሲሆን የተገኙት መረጃዎች በዓይነታዊ የምርምር ዘዴዎች ተተንትነዋል፡፡በጥናቱ ሰነድ ፍተሻና ቃለመጠይቅ ጥቅም ላይ የዋሉ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ናቸዉ፡፡ጥናቱን ለማካሄድ በተተኳሪዎቹ መማሪያ መጻሕፍት ዉስጥ የተካተቱ የሰዋስዉ ትምህርት ይዘቶችን ለይቶ በማዉጣት በክለሳ ድርሳን ክፍል የቀረቡትን Larsen Freeman(1991)፣ Harmer(1991) እና Ur(1996)የሚያራምዷቸዉን ንድፈ ሀሳባዊ መሰረቶችን በመመርኮዝ ትንተና ተሰጥቶባቸዋል፡፡በጥናቱ የተገኘዉ ዉጤት እንደሚያመለክተዉ የይዘቶች አቀራረብን በተመለከተ በታላሚዎቹ መማሪያ መጻሕፍት ዉስጥ ከአጠቃላይ ወደ ዝርዝር የአቀራረብ ስልት ያልተካተተ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ዉጤት ተኮር በሆነ ስልት የቀረቡት ይዘቶች ሂደት ተኮር በሆነ ስልት ከቀረቡት ይዘቶች አብላጫዉን እንደሚይዙ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ከአደረጃጀት አንጻር ደግሞ አብዛኛዎቹ ሰዋስዋዊ መልመጃዎች በተለያዩ ምዕራፎች እየተደጋገሙ መቅረባቸዉን ጥናቱ አሳይቷል፡፡ነገር ግን በርካታ ይዘቶች ስፋትና ጥልቀታቸዉን ሳይጨምሩ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ተደራጅተዉ መቅረባቸዉን ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ይሁን እንጂ በተተኳሪዎቹ መጻሕፍት ዉስጥ የተካተቱት የሰዋስዉ ትምህርት ይዘቶች ከሰዋስዉ ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት መርሆዎች አኳያ ሲፈተሹ ሰዋስዋዊ ይዘቶቹ በምሳሌዎች እየታገዙ መቅረባቸዉና በተለያዩ ምዕራፎችና ክፍሎች እየተከታተሉ መደራጀታቸዉ ከጠንካራ ጎናቸዉ መካከል የሚጠቀስ ሲሆን አብዛኛዎቹ ይዘቶች ደግሞ ጥልቀታቸዉን ሳይጨምሩ መደራጀታቸዉ እንደ ደካማ ጎን ታይተዋል፡፡ በመሆኑም የታዩት ደካማ ጎኖች ወደፊት መጻሕፍቱ በሚሻሻሉበት ወቅት እንዳይደገሙና ጥንቃቄ እንዲደረግ አጥኝዋ ለመጠቆም ትወዳለች፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title በደቡብ ክልል ሥራ ላይ ባሉ የ5ኛና 6ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጻሕፍት ውስጥ የተካተቱ የሰዋስው ትምህርት ይዘቶች አቀራረብና አደረጃጀት ግምገማ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account