Jimma University Open access Institutional Repository

የአንብቦ መረዳት መልመጃዎች የይዘት አዘገጃጀትና አቀራረብ ፍተሻ (በ2007 ዓ.ም በታተመው የ5ኛ ክፍል እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ የአማርኛ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የቀረቡ ይዘቶች ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author ይመኙሻል ቀለታ
dc.contributor.author ምህረት ሳዳም
dc.contributor.author አብዱ ራህማን ፋንታሁን
dc.date.accessioned 2022-02-24T13:23:07Z
dc.date.available 2022-02-24T13:23:07Z
dc.date.issued 2014
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/6490
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ በ2007 ዓ.ም በታተመው የ5ኛ ክፍል የአማርኛ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የቀረቡ የአንብቦ መረዳት መልመጃዎች አዘገጃጀትና የክፍል ውስጥ አተገባበር ፍተሻ ነው፡፡ ጥናቱ ገላጭ የምርምር ንድፍን የተከተለ ሲሆን በሰነድ ፍተሻና በቃለ መጠይቅ መረጃዎች ተሰብስበዋል፡፡ በጥናቱ አስፈላጊ መረጃዎችን ለመሰብሰብ አምስት መምህራን በጠቅላይ የንሞና ዘዴ ተመርጠው ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸዋል፡፡ የተሰበሰበው መረጃ በአግባቡ ተደራጅቶ ትንተና ተደርጎበታል፡፡ ከመረጃዎቹ የተገኙት ውጤቶች የሚያመለክቱት የአንብቦ የመረዳት መልመጃዎች የይዘት አቀራረብ ለመማር ማስተማሩ ሂደትም ሆነ ለተማሪዎቹ ልምምድ አመቺ መሆናቸውን፤ አንብቦ የመረዳት መልመጃዎች የመጽሐፍ አቀራረብ ተገቢነት፣ የተማሪዎችን ደረጃ፣ ዕድሜና ችሎታ እንዲሁም ዳራዊ እውቀታቸውን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገቡ መሆናቸውን፤ የመማሪያ መጽሐፉ አንብቦ የመረዳት መልመጃዎች በተቀናጀ መልኩ እንደተዘጋጁና የማስተማሪያ መሳሪያዎቹ አንብቦ የመረዳት ክሂሎችን ለማስተማር እገዛ እንዳላቸው የጥናቱ ውጤት ያመለክታል፡፡ በአንጻሩ የአንብቦ መረዳት መልመጃዎች አቀራረብ ለትምህርቱ ከተመደበው ሰዓት ጋር ያለመጣጣም ችግሮች መኖራቸውን፣ አልፎ አልፎ ስለ መልመጃዎቹ አሰራር ሙሉ መረጃ የማይሰጡ መመሪያዎች በመጽሐፉ ውስጥ መካተታቸውን የጥናቱ ውጤት አሳይቷል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title የአንብቦ መረዳት መልመጃዎች የይዘት አዘገጃጀትና አቀራረብ ፍተሻ (በ2007 ዓ.ም በታተመው የ5ኛ ክፍል እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ የአማርኛ መማሪያ መጽሐፍ ውስጥ የቀረቡ ይዘቶች ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account