Jimma University Open access Institutional Repository

ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ የተማሪዎችን የመፃፍ ክሂል ለማዳበር እና ተነሳሽነትን ለመፍጠር ያለው ሚና (በአፋን ኦሮሞ አፋቸውን በፈቱ 10ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት)

Show simple item record

dc.contributor.author መስታዎት ተስፋዬ
dc.contributor.author ሙሃመድ ጀማል
dc.contributor.author ለማ ንጋቱ
dc.date.accessioned 2022-04-12T11:51:00Z
dc.date.available 2022-04-12T11:51:00Z
dc.date.issued 2014
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/7027
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ ተግባር ተኮር የአማርኛ ቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ አፍ ፈት ያልሆኑ ተማሪዎችን የመፃፍ ክሂል ያለውን ሚና መመርመር ነው፡፡ ይህ ጥናት በዋናነት ፍትነታዊ ንድፍን የተከተለ ሲሆን መጠናዊና አይነታዊ ወይም ቅይጥ ስልትን መሰረት አድርጎ ቀርቧል፡፡ የጥናቱ ተተኳሪዎችም የእጣ ንሞና ዘዴን መሰረት በማድረግ ተመርጠዋል፡፡ ተሳታፊዎችም ነጌሌ አርሲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2013 ዓመተ ምህረት የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችና የአማርኛ ቋንቋ መምህራን ናቸው፡፡ በመሆኑም በተመረጠው የናሙና ስልት 88 ተማሪዎች ለጥናቱ ተመርጠዋል፡፡ መረጃዎች በጽሁፍ መለኪያ ፈተና፣ በጽሁፍ መጠይቅና በምልከታ ተሰብስበዋል፡፡ መረጃዎቹም በመጠናዊና አይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ስልትን በመከተል SPSS Vers t i on 20 ሶፍትዌርን በመጠቀም በቡድናዊ ገላጭና በጥንድ የናሙና ቲ- ቴስት ከተተነተኑ በኋላ በገላጭ መንገድ ውጤቱ ተብራርቶ ቀርቧል፡፡ በሁለቱ መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች የተገኙት መረጃዎች የቁጥጥር ቡድን የቅድመ ፈተና በአማካይ ውጤት (M= 56 .47 , SD=14.607) ድህረ ፈተና (M= 56.68 . SD= 14.37) ሲሆን የሙከራ ቡድን ቅድመ ፈተና (M= 56.52፣ SD=10.21) ድህረ ፈተና (M= 66.34 SD= 9.10) መሆኑን የሙከራ ቡድኑ ሲያመለክት የቁጥጥርና የሙከራ ቡድኑ አጠቃላይ አማካይ የቅድመ ፈተና የጽሑፍ መጠይቅ (M= 3 .10) እና የሙከራ ቡድን (M= 3 .07) ሲሆን፣ የቁጥጥርና የሙከራ ቡድኑ አጠቃላይ አማካይ የድህረ ፈተና የጽሑፍ መጠይቅ (M= 3 .13) እና የሙከራ ቡድን አጠቃላይ(M= 3 .78) ሆኗል፡፡ በጥንድ ናሙና ቲ- ቴስት በተደረገው መተንተኛ መሰረት ደግሞ የሙከራና የቁጥጥር ቡድን የቅድመ ትምህርት የተነሳሽነት ደረጃ ልዩነት የ25ቱ ተለዋዋጭ ( t= 0 .1754, p=0.864) ሲሆን በሁለቱ ቡድን መካከል ጉልህ ልዩነት አለመኖሩን ያመለክታል፡፡ የድህረ ትምህርት የተነሳሽነት ደረጃ ልዩነት የ25ቱ ተለዋዋጭ ( t= 5 .147, p=0.042) ሲሆን በሁለቱ ቡድን መከካከል ጉልህ ልዩነት መኖሩን ያመለክታል፡፡ በመሆኑም ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ የመፃፍ ተነሳሽነትን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡ ፡ ማሳያውም የቅድመ የሙከራና የቁጥጥር ቡድን ልዩነት ነው፡፡ የጥናቱ ውጤትን መሰረት በማድረግ የቋንቋ መምህራን የጽሁፍ ክሂልን በሚያስተምሩበት ወቅት የተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማር ዘዴን ቢጠቀሙ፣ መምህራን የጽሁፍ ንሑሳን ክሂሎች ላይ የበለጠ ትኩረት ቢያደርጉ የሚል ሀሳብ ተሰጥቷል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ የተማሪዎችን የመፃፍ ክሂል ለማዳበር እና ተነሳሽነትን ለመፍጠር ያለው ሚና (በአፋን ኦሮሞ አፋቸውን በፈቱ 10ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት) en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account