Jimma University Open access Institutional Repository

የመጀመሪያ ጊዜ የወር አበባ አቀባበል ሥርዓተ ክወና (ድግትስ ጋሕጃ) ትንተና፤ በጉሙዝ ብሔረሰብ ተተኳሪነት፤

Show simple item record

dc.contributor.author አበበ ጥላሁን ወንድማገኝ
dc.contributor.author ማንያለው አባተ
dc.date.accessioned 2022-04-15T12:15:01Z
dc.date.available 2022-04-15T12:15:01Z
dc.date.issued 2014
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/7144
dc.description.abstract ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ የመጀመሪያ ጊዜ የወር አበባ አቀባበል ሥርዓተ ክወና (ድግትስ ጋህጃ) ትንተና፤ በጉሙዝ ብሔረሰብ ተተኳሪነት፤ በሚል ርዕስ የቀረበ ነው፡፡ የጥናቱ ዓላማ የጉሙዝ ብሔረሰብ የመጀመሪያ ጊዜ የወር አበባ አቀባበል ሥርዓተ ክዋኔን መተንተን ነው፡፡ ይህንና ሌሎች ዝርዝር ዓላማዎችን ለማሳካት ክዋኔ ተኮር ንድፈ ሀሳብን ተከትሎ በመከወን፣ ቁልፍ መረጃ አቀባዮችን ዕድል የማይሰጥ የንሞና ዘዴ አካል በሆነው በታላሚ ናሙና ስልት ተመርጠዋል፡፡ የድርሳናት መረጃዎችን ከቤተ መጻሕፍት፣ የክወና መረጃዎች በምልከታ፣ በቃለ-መጠይቅ እና በተተኳሪ የቡድን ውይይት ተሰብስቧል፡፡ ጥናቱ ከማኅበረሰቡ ማኅበራዊ፣ ሥነ ልቡናዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ሥርዓተ ጾታዊ እና እንስታዊ ምልከታ ጋር በማገናኘት የተተነተነ በመሆኑ ዓይነታዊ የምርምር መተንተኛ ላይ አተኩሮ ገላጭ የምርምር ስልትን መጠቀም ተችሏል፡፡ ጥቅል የዲስኩር እና የትዕምርት ትንተና ሂደት ተተግብሯል፡፡ በተገኘው ውጤት መሠረት የጉሙዝ ብሔረሰብ የመጀመሪያ ጊዜ የወር አበባ አቀባበል ሥርዓተ ክወና የመከሰቻ አጋጣሚው፣ የሥነ ልቡና፣ የመከወኛ ቦታ፣ ቁሳቁስ፣ አልባሳት፣ ጌጣጌጥ እና የምግብና የመጠጥ ዝግጅቶችን ያደርጋሉ፡፡ በማኅበራዊ ደረጃና በፆታ የአከዋወን ልዩነቶች መኖራቸውን ለማየት ተችሏል፡፡ ብሔረሰቡ ለመጀመሪያ ጊዜ የወር አበባ አቀባበል ሥርዓት (ድግትስ ጋህጃ) ያለው ምልከታና የሚሰጠው ቦታ ከፍ ያለ መሆኑን፤ ይህ አጋጣሚ ማኅበራዊ ትስስሩን እና ሥነ ልቡናዊ ከፍታውን የሚያጠናክርበት፣ የሥነ ተፈጥሮን ነጻነት የሚያውጅበት፣ ለሴት ልጅ ያለውን ክብር የሚገልጽበት፣ ልዩ ልዩ ዕሴቶቹን እና እምነቱን የሚያፀናበት መንፈሳዊ የመሸጋገሪያ ከበራ መሆኑን አሳይቷል፡ en_US
dc.language.iso other en_US
dc.title የመጀመሪያ ጊዜ የወር አበባ አቀባበል ሥርዓተ ክወና (ድግትስ ጋሕጃ) ትንተና፤ በጉሙዝ ብሔረሰብ ተተኳሪነት፤ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account