Jimma University Open access Institutional Repository

በኢሉአባቦር ዞን በሁሩሙና በሶንጣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸዉ ተነሳሽነትና የዉጤት ተዛምዶ

Show simple item record

dc.contributor.author ተስፋዬ ኦላና
dc.contributor.author በቃሉ ፈረደ
dc.contributor.author መሀመድ ጀማል
dc.date.accessioned 2022-04-15T12:49:45Z
dc.date.available 2022-04-15T12:49:45Z
dc.date.issued 2014
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/7147
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና ትኩረት የአፋን ኦሮሞ አፈ-ፈት ተማሪዎች አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት ለመማር ያላቸውን ተነሳሽነትና የትምህርት ውጤት ተዛምዶ መፈተሸ ነው፡፡ ጥናቱ የተካሄደው በኢሉባቦር ዞን በሁሩሙ ወረዳ ሁሩሙ ሁለተኛ ደረጃና በሶንጣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2013 ዓ.ም በመማር ላይ በሚገኙት 110 የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ነው፡፡ በዕድል ሰጪ የናሙና አመራራጥ ዘዴ ከተመረጡት ተማሪዎች በጽሑፍ መጠይቅና በፈተና የጥናቱ መረጃዎች ተሰብሰበዋል፡፡ በገላጭ ስታቲሲቲክሶችም ተተንትኖ የተብራራ ሲሆን በመረጃው ትንተና መሠረት በተማሪዎቹ አማርኛን በሁለተኛ ቋንቋነት የመማር ተነሳሽነትና በቋንቋው ትምህርት ውጤት መካካል የጎላ ተዛምዶ አልታየም፡፡ በተነሳሽነት አይነቶችና በአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ውጤት መካከልም ተዛምዶ አልታየም፡፡ ይሁን እንጂ በሁለተኛ ቋንቋ (አማርኛ) የመማር ተነሳሽነት በፆታ መካከል ተዛምዶ ታይቷል፡፡ የሁለተኛ ቋንቋ ተነሳሽነት በትህምርት ቤትና በትምህርት ቤት መካከልም የውጤት ልዩነት አሳይቷል፡፡ ከጥናቱ ውጤት በመነሳት ሁለተኛ ቋንቋ የሚያስተምሩ መምህራን ትምህርቱን ሲያቀርቡ የተማሪዎችን ፍላጎትና ስሜት በሚያነሳሳ መልኩ ቢያቀርቡ፣ ሴቶችም ሆነ ወንዶች ተማሪዎች ምን አይነት ማበረታቻ ቢደረግላቸው ውጤታማ እንደሚሆኑ አስቀድሞ በማወቅ የተማሪዎችን የመማር ተነሳሽነት ለማጠናከር የሚረዱ ተግባራትን ቢያከናውኑና ይህንኑ መሠረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል ቢያደርጉ የተማሪዎቹ የሁለተኛ ቋንቋ ትምህርት (አማርኛ ቋንቋ ትምህርት) ተነሳሽነት ሊሻሻል ይችላል የሚሉ የመፍትሔ ሀሳቦች ተጠቁመዋል፡፡ en_US
dc.language.iso other en_US
dc.title በኢሉአባቦር ዞን በሁሩሙና በሶንጣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ለአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ያላቸዉ ተነሳሽነትና የዉጤት ተዛምዶ en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account