Jimma University Open access Institutional Repository

በጅማ ዞን ጅማ ከተማ የሚገኙ የፌደራል መስሪያ ቤቶች የሚጽፏቸው የሥራ ደብዳቤዎችና ማስታወቂያዎች ላይ የሚታዩ ስህተቶች ትንተና

Show simple item record

dc.contributor.author ዝናሽ, ተሰማ
dc.contributor.author ጥበቡ, ሽቴ
dc.contributor.author ማንያለው, አባተ
dc.date.accessioned 2023-03-03T07:54:48Z
dc.date.available 2023-03-03T07:54:48Z
dc.date.issued 2014-08
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/7982
dc.description.abstract የዚህ ጥናት አብይ ዓላማ በፌደራል መስሪያቤቶች የስራደብዳቤዎች እና ማስታወቂያዎች ላይ የሚታዩትን ስህተቶችና የስህተት ምንጮችን መለየት ነው፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካትም ገላጭ የምርምር ስልት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ጥናቱ አመቺ ናሙና ዘዴን በመጠቀም የጉሙሩክ፣ የገቢዎች፣ የኢትዮ ቴሌኮም፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ፌደራል መስሪያ ቤቶች ላይ የተካሄደ ነው፡፡ መረጃዎች በሰነድ ፍተሻ እና በቃለ መጠይቅ የተሰበሰቡ ሲሆን፤ የሰነድ ፍተሻው የፌደራል መስሪያ ቤቶቹ በሚጽፏቸው ደብዳቤዎችና ማስታወቂያዎች ስህተቶች ላይ ሲሆን የቃለ መጠይቁ ደግሞ የስህተት ምንጮችን መረጃ ለመሰብሰብ አገልግሏል፡፡ ከተጠኚ መስሪያ ቤቶቹ ውስጥ የተገኙት ስህተቶች ተቆጥረውና በመቶኛ ተሰልተው ሲተነተኑ የስህተት ምንጮችም ተለይተው ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ግኝትም የፌደራል መስሪያ ቤቶቹ ደብዳቤና ማስታወቂያ በሚጽፉበት ጊዜ የቋንቋ አጠቃቀም፣ የዐ. ነገር አወቃቀርና የስርአተ ነጥብ አገባብ ዋና ዋና ስህተቶችን እንደሚፈጽሙ አሳይቷል፡፡ በቋንቋ አጠቃቀም ስህተት ውስጥ ሌሎችን ንኡሳን ስህተቶች እንደ የፊደል አጻጻፍ ፣ ግድፈት ፣ የቃላት ጭመራ ፣ የቃላት አመራረጥ እና የድግግሞሽ ስህተቶች ተፈጽመዋል፡፡ በዐ. ነገር አወቃቀር ምድብ ውስጥ ደግሞ የመስተዋድድ አገባብ ፣ የመደብ አለመስማማት፣ የተሳቢ አጠቃቀም እና የቁጥር አለመስማማት ንኡሳን ስህተቶች ተለይተዋል፡፡ በስርአተ ነጥብ አገባብ ስር ያሉ ንኡሳን ስህተቶች፡- የአራት ነጥብ አጠቃቀም ፣ ድርብ ሰረዝ አገባብ እና ነጠላ ሰረዝ ስህተቶች እንደ ቅደም ተከተላቸው ከከፍተኛው ወደ አነስተኛው ተለይተው ተቀምጠዋል፡፡ ለነዚህም በቃለ መጠይቅ የተገኙት ዋነኛ የስህተት ምንጮች፡- ስነ ልቦናዊ ችግር፣ የቋንቋ ስርዓትና ባህሪያቱ፣ የኮምፒውተር ክህሎት፣ በቋንቋው የመጻፍ ፍላጎትና ተነሳሽነት፣ የተጻፉትን ጽሁፎች ደጋግሞ አለማንበብና ግለ ሂስ ያለ ማስቀመጥ ችግር እንደሆኑ ተለይቷል፡፡ በአጠቃላይ መስሪያቤቶቹ የተለዩት የስህተት ምንጮች ላይ መስራት እንዳለባቸው ያሳየ ነው፡፡ ስለዚህ የሚመለከተው አካል አስተዋጽኦ እንዲያደርግና መስሪያቤቶቹም ትኩረት ሰጥተው የተቋማቸውን ገጽታ በሚጻፉ ጽሁፎች ላይ ከፍ ማድረግ ቢችሉ ፤ የበኩላቸውን ጥረት ቢያደርጉ የተሻለ ነው፡ ፡ en_US
dc.language.iso en en_US
dc.subject ደብዳቤዎች en_US
dc.subject ማስታወቂያዎች en_US
dc.subject ስህተት en_US
dc.subject ምንጭ en_US
dc.subject ትንተና en_US
dc.title በጅማ ዞን ጅማ ከተማ የሚገኙ የፌደራል መስሪያ ቤቶች የሚጽፏቸው የሥራ ደብዳቤዎችና ማስታወቂያዎች ላይ የሚታዩ ስህተቶች ትንተና en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account