Jimma University Open access Institutional Repository

ስነ ምግባራዊ ሂስ በተመረጡ አጫጭር ልቦለዶች ዉስጥ ማሳያነት የኢትዮጵያ ስነ-ጹሑፍና ፎክሎር ሁለተኛ ዲግሪ ማሟያነት

Show simple item record

dc.contributor.author ጌታቸዉ አየነዉ
dc.contributor.author ማንያለዉ አባተ
dc.contributor.author ምህረት ሳዳሞ
dc.date.accessioned 2023-10-05T08:19:44Z
dc.date.available 2023-10-05T08:19:44Z
dc.date.issued 2015
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/8508
dc.description.abstract ሥነ‐ምግባራዊ ሂስ” በተመረጡ አጫጭር ልቦለዶች ውስጥ በሚል ርዕስ የቀረበው ይህ ጥናት በአምስቱ የሱለይ አደም ድርሰቶች ውስጥ የስነ‐ምግባር ሂስን መመርመር ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡ ስነ ጹሑፍ በዘመን መንፈስ ዉስጥ የራሱን ጭብጥ እየያዘ እራሱንም በተለያዬ የአጸጻፍ ስልቶች እያሳደገ የማህበረሰቡን ተጨባጭ ህይወትና ኑሮ መልሶ ለማህበረሰቡ ያቀርባል፡፡በጊዜ ሄደትም የስነ ጹሑፍ ሂስ ጭብጥን መሰረት በማድረግ ማጠንጠኛ ከሆኑት መካከል ስነ ምግባራዊ ሂስ አንዱ ሁኖ የሚጠቀስ ነዉ፡፡ ለዚህም የሂስ ዓይነት በጥናቱ ዉስጥ የሞራልን ንድፈ ሀሳብ መነሻ አድርጎ የዲኦንቶሎጂን ንድፈ ሀሳብ በዋናነት፣ ቴሊኦሎጅ እና ቨርቹ ኤቲክስ የሚባሉትን ዘረፎችም እንደ አስፈላጊነታቸው ጥቅም ላይ አውሏል፡፡ እኩይና ሰናይ ድርጊት፣ ግብረገባዊነት፣ ማህበራዊ እሴቶች፣ የሰዉ ባህሪና ፀባይ፣ኅሊናና ሀቀኝነትን ማጉደል እና የክብር መውረድ የሚሉትን ጽንሰ ሀሳቦች እንደ አንድ የስነ‐ምግባራዊ ሂስ ከሚዳስሳቸዉ ጉዳዮች ማሳያ በመውሰድ እንዴት፣ የት፣ መቼ፣ በምን፣ ለምን እና በነማን መገለጫነት እንደቀረበ ለማሳየት ሞክሬያለው፡፡ በዚህም በልቦለዶቹ ውስጥ የሰው ልጅ ሲያዳብረው የመጣን ደንበኛውን የስነ‐ምግባራዊ እሴት እንደ ኋላ ቀር፣ ከንቱና ቆላፊ አድረገው የሚመለከቱ ገጸ ባህሪያት ከማህበረሰቡ ህግና ደንብ አፈንግጠዉ በመዉጣት እኩይ የሚባሉ ድርጊቶችን እንደሚፈጸም አመላክቻለሁ፡፡ በስሜት መዘውርነት ድርጊት መፈጸማቸው ደግሞ “በእኩይ ባህሪ በመታነጽ ከሰዉነት የወጣ አረመኔያዊ ጭካኔ በተሞላበት ከኅሊና ዉጭ እና በሌላዉ ስቃይ የሚደሰቱና በተግባሩም የሚሰተፉ ገጸ ባህሪያት እንዳሉ ታይቷል፡፡ በአንድ ጎራ ወጣት ትውልዶች ከነባሩ የስነ‐ምግባር እሴት እንውጣ በሚል ሲሞግቱ፣ በሌላኛው ጎራ የወጣቶችን ከማንነት መውጣት ለመታደግ ሲጥር፣ በልቦለዶቹ ፈጠው የሚታዩትን ክሱቶችና ሁነቶች ከሚፈጽሙት ገጸ ባህሪያት በግልባጩ የመፍትሄ ጥበብን የሚያዘጋጁ ገጸ ባህሪያት ያሉ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡ ትልቅ አክብሮትና እምነት የተጣለባቸው የእምነት አባቶች በላይ በአብሮነት ለመኖር፣ ሀይማኖትም ይሁን ሌሎች የግል ጉዳዮች ሳይገድቦቸዉ፣ አንዱ ለአንዱ በመተሳሰብና በመተዛዘን፣ ያላቸዉን በማካፈልም ይሁን በመረዳዳት፣ ኢትዮጵያዊ ስነ ምግባርን በመጠበቅ ደረጃ ላቅ ያለ ሚና ሲወጡ ተስተውሏል፡፡ በዚህም ተግባር ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከህጻናት እስከ አዛውንት አድነናቆትን ሲቻሩና ሲሞገሱ በተቃራኒዉ እኩይ ድርጊትን ሲተገብሩ በማህበረሰቡ ሲወገዙና ሲንቋሸሹ ያሰያል፡፡ ብዙዎቹ ገጸ ባህሪያት ትናንት በተሸመነ የዛሬ ማንነት፣ ዛሬም ለነገ ለቀጣይ ትዉልድ ቅብብሎሽ እርሹ በሚይዝበት መልኩ፣ በማህበረሰቡ ተወደዉና በምሳሌነት እየተጠቀሱ ቆመው ህይወትን ሲገፉ ተስተውለዋል፡፡ ለሁሉም የስነ ምግባራዊ ሂስ ማሳያ የሆነውን የአጭር ልቦለድ መድብል ያለምንም ግርዶሽ ሱለይ አደም በጥበብ ወዝ አሳይቷል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title ስነ ምግባራዊ ሂስ በተመረጡ አጫጭር ልቦለዶች ዉስጥ ማሳያነት የኢትዮጵያ ስነ-ጹሑፍና ፎክሎር ሁለተኛ ዲግሪ ማሟያነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account