Jimma University Open access Institutional Repository

ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋን በሁለተኛ ቋንቋነት ለመማር ያላቸው ተነሳሸነት ከአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር ያለው ተዛምዶ በሁሩሙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ10ኛ ክፍል ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author ፈንታነሸ ጌቴ
dc.contributor.author ማንያለዉ አባተ
dc.date.accessioned 2023-10-05T09:01:03Z
dc.date.available 2023-10-05T09:01:03Z
dc.date.issued 2015
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/8510
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ የመማር ተነሣሽነት ከአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር ያለውን ተዛምዶ በ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት መፈተሽ ነው፡፡ የጥናቱን አላማ ለማሳካትም ተዛምዷዊ የምርምር ስልት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ጥናቱ በአመቺ የንሞና ዘዴ በተመረጠ በሁሩሙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተካሄደ ነው፡፡በተጨማሪም የ10ኛ ክፍልን በአላማ ተኮር የንሞና ዘዴ በመጠቀም የዚህ ጥናት ተተኳሪዎች ሆነዋል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎችም በእኩል እድል ሰጪ የንሞና ዘዴ የተመረጡ 97 የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ የመማር ተነሳሽነታቸው አማካይ ውጤት 3.027 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የተማሪዎቹ የመማር ተነሣሽነት መደበኛ ልይይት0.36814 ሲሆን የእያንዳድ ተጠኚ ምላሽ አማካይ ውጤት ርቀቱ ጠባብና የማያዋዥቅ ሲሆን ተማሪዎች ከውስጣዊ ተነሣሽነት የበለጠ ለውጫዊ ተነሣሽነት ትኩረት የሰጡ ሲሆን ጉልህ ልዩነት ግን እንደሌለ በባድ ናሙና ፍተሻ ተረጋግጧል፡፡ ዉጤቱም 0.76 ሆኖ ተመዝገቧል፡፡ የተማሪዎቹ አንብቦ መረዳት ችሎታ በአማካይ ውጤታቸው ተሰልቷል፡፡ በተማሪዎች የመማር ተነሣሽነትና በአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በእስታቲክስ፣ በፒርሰን የተዛምዶ መለኪያ ተሰልቷል፡፡ የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየውም የተማሪዎቹ አንብቦ መረዳት ችሎታ አማካይ ውጤት(53.938) መሆኑ በናሙና ፍተሻ ተረጋግጧል፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ የአንብቦ መረዳት ችሎታ አለ ለማለት አያስደፍርም፡፡ በመማር ተነሳሽነትና በአንብቦ መረዳት ፈተና ውጤት መካከልም አዉነታዊ ተዛምዶ አልታየም፡፡ ውጤቱም (r= -049 የ"P" ዋጋ 0.852 ወይም P > 0.5) በመሆኑ አሉታዊ ተዛምዶ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋን በሁለተኛ ቋንቋነት ለመማር ያላቸው ተነሳሸነት ከአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር ያለው ተዛምዶ በሁሩሙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ10ኛ ክፍል ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account