Jimma University Open access Institutional Repository

በአፋን ኦሮሞ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታና የንባብ ፍጥነት ተዛምዶ በዘጠነኛ ክፍል ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author ታሪኳ የማታ
dc.contributor.author ማንያለው አባተ
dc.contributor.author ምህረት ሳዳሞ
dc.date.accessioned 2023-11-08T08:06:55Z
dc.date.available 2023-11-08T08:06:55Z
dc.date.issued 2015
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/8782
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ትኩረት በአፋን ኦሮሞ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታና የንባብ ፍጥነት ተዛምዶ በዴዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት መፈተሽ ነው፡፡ ጥናቱ በተዛምዷዊ የምርምር ንድፍ ላይ ተመርኩዟል፡፡ ካሉት የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አመቺ ንሞና ዘዴን በመጠቀም ዴዶ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመረጠ ሲሆን የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች የዚህ ጥናት ተተኳሪ የተደረጉት በአላማ-ተኮር ናሙና ዘዴ ነው፡፡ በ30 ፐርሰንት ተጠኚዎች ቢመረጡ በቂ እንደሆነ በማሰብ ከሰባት የ9ኛ መማሪያ ክፍሎች በቀላል እጣ ንሞና ዘዴ 116 ተማሪዎችን በማውጣጣት የጥናቱ ተሳታፊ ተደርገዋል፡፡ የተጠኚዎቹ በአማርኛ ቋንቋ አንብቦ የመረዳት ችሎታ ከማንበብ ፍጥነት ጋር ያለው ተዛምዶ ምን እንደሚመስል ለማወቅ ፈተና ዋንኛው የመረጃ መሰብሰቢያ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ጥናቱ አንብቦ የመረዳት እና የማንበብ ፍጥነት መለኪያ ፈተና ተጠቅሟል፡፡ በሁለቱም መረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎች የተገኙ እስታቲስቲካዊ ውጤቶች ትንተናና ማብራሪያ ቀርቦባቸው ግኝቶቹ ተመላክተዋል፡፡ የጥናቱ ግኝት እንዳመለከተው የተተኳሪዎቹ አንብቦ የመረዳት ችሎታ አማካይ ውጤት ከሚጠበቀው በታች ወይም በጣም ዝቅተኛ (9.569/ 20) መሆኑ በተማሪዎቹ አንብቦ የመረዳት ብቃት ችግር እንዳለ አመላክቷል፡፡ በጥናቱ ግኝት መሰረት ከአጋማሹ (50%) በታች ያገኙ ተጠኚዎች አጠቃላይ ብዛት 56 (48.27%) ሲሆን ይህም የሚያመለክተው ከተጠኚዎቹ ከፊሎቹ ተማሪዎች በንባብ ፍጥነት ፈተናው ማለፊያ ማርክ ማግኘት እንዳልቻሉ የሚያሳይ ነው፡፡ ልክ በአንብቦ መረዳቱ እንደተመዘገበው ውጤት ሁሉ በጣም ከፍተኛ የሚባል (80% እና በላይ) የማንበብ ፍጥነት ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር በጣም ውሱን 3 (2.59%) ብቻ መሆኑ የሚያመለክተው በአብዛኛው በሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎቹ ዘንድ ከፍ ያለ የንባብ ፍጥነት ችግር መኖሩን ጠቋሚ ነው፡፡ በተጠኚዎቹ አንብቦ የመረዳት ችሎታ እና የንባብ ፍጥነት መካከል ቀጥተኛ በሆነ መንገድ በባለ ሁለት ጫፍ ትይዩ የሆነ አሉታዊ ተዛምዶ (rxy -0.057) እንደሚታይ እስታቲስቲካዊ መረጃው ያመለክታል፡፡ ይህም ማለት የተጠኚዎቹ የንባብ ፍጥነት ሲቀንስ በዚያው ልክ የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውም መቀነስ እንደሚያሳይ ተረጋግጧል፡፡ በዚህ መሰረት የሁለተኛ ቋንቋ ተማሪዎቹ የንባብ ፍጥነት እና የማንበብ ብቃት በአዝጋሚ ደረጃ ላይ መገኘት ለአንብቦ መረዳት ችሎታቸው እንደሚጠበቀው አለመጎልበት ወይም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ መሆን እንደ አንድ ወሳኝ ችግር ሊቆጠር የሚችል ጉዳይ መሆኑን መገመት ተችሏል፡፡ የጥናቱን ግኝቶች መሰረት በማድረግ እና በክለሳ ድርሳናት በመታገዝ የመፍትሄ ሃሳቦች ተመላክተው ጥናቱ ተጠቃሏል፡፡ en_US
dc.language.iso en_US en_US
dc.title በአፋን ኦሮሞ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታና የንባብ ፍጥነት ተዛምዶ በዘጠነኛ ክፍል ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account