dc.contributor.author | ነኢማ ኑሩ | |
dc.contributor.author | ማንያለው አባተ | |
dc.contributor.author | ምህረት ሳዳሞ | |
dc.date.accessioned | 2023-11-13T08:17:12Z | |
dc.date.available | 2023-11-13T08:17:12Z | |
dc.date.issued | 2015 | |
dc.identifier.uri | https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/8842 | |
dc.description.abstract | ይህ ጥናት ያተኮረው የሰዋስው ይዘቶችን በአሳታፊ ዘዴ ማስተማር የተማሪዎችን የሰዋስው እውቀት እና የመጻፍ ክሂል ችሎታ ለማሳደግ ያለው ሚና ፍተሻ ላይ ነው፡፡ የጥናቱ ተተኳሪዎች በአመቺ የናሙና ዘዴ የተመረጡት በጅማ ዞን በሲግሞ ወረዳ የአዱ ሲግሞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ ጥናቱ ሙከራዊ የምርምር ንድፍን ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን፣ በተመረጠዉ ትምህርት ቤት በ2015 ዓ.ም ካሉ ሰባት የ10ኛ ክፍሎች መካከል በቀላል እጣ የናሙና ስልት የ10ኛ B እና 10ኛ E ክፍል ተማሪዎች የጥናቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ ቀጥሎም በእጣ መሰረት 10ኛ B የቁጥጥር ቡድን 10ኛ E ክፍል ደግሞ የሙከራ ቡድን መስርተዋል፡፡ በተጠኚዎቹ መካከል የስዋስው ትምህርትና የመጻፍ ክሂል ቅድመ-ግንዛቤ በጥናቱ ውጤት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተጽእኖ ለመከላከል ሲባል በተጠኚዎቹ አንጻራዊ ተቀራራቢ የሰዋስውና አንቀጽ መጻፍ ችሎታ ላይ መመርኮዝ አስፈላጊ በመሆኑ ቅድመ ትምህርት የሰዋስው እና አንቀጽ መጻፍ ፈተና ተሰጥቷቸዉ አንጻራዊ ተቀራራቢ ውጤት ያመጡት 40 /አርባ/ ተማሪዎች የቁጥጥርና የሙከራ ቡድኑ ተተኳሪዎች ተደርገዋል፡፡ ለዚህ ጥናት የመረጃ ምንጭ ሆኖ ያገለገለዉ የሰዋስው እና አንቀጽ መጻፍ ፈተናዎች ናቸው፡፡ ይህም ሰዋስውን በአሳታፊ ዘዴ ማስተማር በተጠኚዎቹ የሰዋስው ግንዘቤና የመጻፍ ክሂል ችሎታ ላይ ያስከተለውን ለውጥ ለመገምገም ጠቅሟል፡፡ የጥናት ውጤቱ እንዳመለከተውም ሰዋስውን በአሳታፊ ማስተማሪያ ዘዴ ድጋፍ የተማሩት የሙከራው ቡድን ተጠኚዎች ስዋስውን በ10ኛ ክፍል አማርኛ መማሪያ መጽሐፍ በቀረቡ ትእዛዛት ማስተማሪያ ዘዴ ከተማሩት የቁጥጥሩ ቡድን ተጠኚዎች የስዋስው ግንዛቤና የመጻፍ ክሂል ችሎታ ጉልህ ልዩነት ያለው (ውጤቱ t= 6.624, df =39, p= .000) መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ p= .000 ከጉልህነት ደረጃ ቋሚ ፓራሜትራዊ እኩልታ ማንጸሪያ p<0.05 የሚያንስ መሆኑ ታውቋል፡፡ በዚህም ሰዋስዉን ከአሳታፊ ዘዴ ጋር በማቀናጀት ማስተማር ከልማዳዊው የስዋስው ማስተማሪያ ዘዴ የተሻለ በሚያደርጉት ተግባራት ላይ የተመሰረተ እና የተማሪዎችን የሰዋስው እውቀትና የመጻፍ ክሒል ለማሻሻል ጠቀሜታ ያለው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ | en_US |
dc.language.iso | en_US | en_US |
dc.title | የሰዋስው ይዘቶችን በአሳታፊ ዘዴ ማስተማር የተማሪዎችን የሰዋስው ችሎታ እና የመጻፍ ክሂል ለማሳደግ ያለው ሚና | en_US |
dc.type | Thesis | en_US |