Jimma University Open access Institutional Repository

በማጃንግ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች ድርሰት ሲጽፉ የሚፈጽሟቸው ስህተቶች እና የስህተት ምንጮች ትንተና (በጋምቤላ ክልል በመጃንግ ዞን በሚገኘው የሰሙይ ትምህርት ቤት 7ኛ ክፍል ተተኳሪነት)

Show simple item record

dc.contributor.author ይማም አህመድ
dc.contributor.author ምህረት ሳዳሞ
dc.date.accessioned 2025-06-25T08:06:38Z
dc.date.available 2025-06-25T08:06:38Z
dc.date.issued 2023-05-18
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/9698
dc.description.abstract የዚህ ጥናት ዋና አላማ በጋምቤላ ክልል በማጃንግ ዞን በጎደሬ ወረዳ በሰሙይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማጃንግ ቋንቋ አፍቸዉን የፈቱ የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች በአማርኛ ድርሰት ሲጽፉ የሚፈጽሟቸውን ስህተቶች፣ የስህተት ምንጮችና የድግግሞሽ መጠን መለየት ነው ፡፡ ይህን ጥናት ከግብ ለማድረስም አጥኝው የተጠቀመዉ የስህተት ምንጮችን ለመለየት አይነታዊ ምርምር ዘዴን የስህተት መጠንና ድግግሞሽን ለመለየት ደግሞ መጠናዊ የምርምር ዘዴን ተጠቅሟል፡፡ የትምህርት ቤት ናሙና አመራረጥ በአመች ናሙና አመራረጥ ተመርጠዋል፡፡ ይህም የአጥኚውን የገንዘብ አቅምና የመረጃ ክፍተት ለመሙላት ምቹ በመሆኑ ነው ፡፡ የክፍል ደረጃ ናሙና አመራረጥ አላማ ተኮር ነው ይህም የሆነዉ አፋቸዉን በማጃንግ ቋንቋ የፈቱ ተማሪዎች አንቀጽ ለመጻፍ የሚደርሱበት ክፍል በመሆኑ ነው ፡፡ ይህም የጽሁፍ ስህተቶችን ገና በ እንጭጩ ለማስወገድ የሚቻልበት የክፍል ደረጃ በመሆኑ ነው፡፡ የመምህራን ናሙና አመራረጥ ደግሞ በትምህርት ቤቱ ሁለት አማርኛ መምህራን ብቻ በመሆናቸው በጠቅላይ ናሙና አመራረጥ ተመርጠው ጥናቱ ተካሂዷል የተማሪዎች ናሙና አመራረጥ በትምህርት ቤቱ በማጃንግ ቋንቋ አፋቸዉን የፈቱ 20 ወንዶችና 30 ሴቶች በድምሩ 50 የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላይ ናሙና ተመርጠው ጥናቱ ተካሂዷል የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎቹ በተማሪዎቹ በተመረጡ ድርሰቶች ፈተናና የጽሁፍ መጠይቅ ተዘጋጅተው ለተማሪዎች በማቅረብ ጥናቱ ተካሂዷል ፡፡ እንዲሁም ለመምህራን የቃለ መጠይቅ በማድረግ የተፈለገዉን መረጃ በመሰብሰብ ለጥናቱ አስፈላጊዉን ግብአት አበርክተዋል ፡፡ በመሆኑም አጥኚዉ የሰበሰበዉን መረጃ በአግባቡና በጥንቃቄ በማዋቀር በአይነታዊና በመጠናዊ የምርምር ዘዴ ተንትኖ ለአንባቢ አቅርቧቸዋል ፡፡ በጥናት ውጤቱ መሰረትም የተተኳሪ ተማሪዎቹ የስህተት ምንጮች የአፍ መፍቻ ቋንቋ ተጽእኖ፣ የዉስጥ ቋንቋ ተጽዕኖ፣ የማስተማሪያ መሳሪያዎች አመራረጥና የማስተማር ዘዴዎች ድክመት፣ የማህበራዊና ስነልቦናዊ ጉዳዮች የሚሉት ነጥቦች ዋናዋናዎቹ እንደሆኑ ተረጋግጧል፡፡ በመጨረሻም አጥኚዉ ለችግሮቹ መፍትሄ ማፈላለግ ላይ የሚመለከታቸዉ አካላት ሁሉ የበኩላቸዉን ድርሻ እንዲወጡ አደራ በማለትና የግል አስተያየቱን በመስጠት ጥናቱን አጠናቋዋል፡፡ en_US
dc.language.iso other en_US
dc.title በማጃንግ ቋንቋ አፋቸውን የፈቱ ተማሪዎች ድርሰት ሲጽፉ የሚፈጽሟቸው ስህተቶች እና የስህተት ምንጮች ትንተና (በጋምቤላ ክልል በመጃንግ ዞን በሚገኘው የሰሙይ ትምህርት ቤት 7ኛ ክፍል ተተኳሪነት) en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account