Abstract:
የዚህ ጥናት አላማ አማርኛን በሁሇተኛ ቋንቋነት የሚማሩ የኦሮምኛ አፍ ፈት ተማሪዎች ተነሳሽነትና
አመሇካከት ከማዳመጥ ክሂል ጋር ያላቸው ተዛምዶ መፈተሽ ነው፡፡ በጅማ ዞን ቀርሳ ወረዳ ሰርቦ
ሁሇተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2015 በ10ኛ ክፍል ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ
ተማሪዎች በአመቺ ንሞና ዘዴ የጥናቱ ተተኳሪዎች ተደርገዋል፡፡ ይህን ጥናት ከግብ ሇማድረስ
የተመረጠው ተዛምዷዊ የምርምር ስልት ሲሆን፣ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች የዚህ ጥናት ተተኳሪ
የተደረጉት በአላማ-ተኮር ንሞና ዘዴ ነው፡፡ ሇዚህ ጥናት ከተጠኚ ተማሪዎች መረጃ ሇመሰብሰብ
ያገሇገሇው የውስብስብ የእጣ ንሞና ዘዴ አካል የሆነው ረድፋዊ የንሞና ዘዴ (systematic sampling)
ነው፡፡ ይህን የናሙና መምረጫ ዘዴ ስራ ላይ በማዋል ከእያንዳንዱ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ያሇ ምንም
ተጨማሪ ቅድመ-ሁኔታ በእኩል እድል ተመርጠው ወደ መረጃ አቀባይነት የሚመጡበትን ስልት ጥናቱ
ተከትሏል፡፡ በዚህ መሰረት በተመጠነ ርቀት በስም መጥሪያ ላይ ስማቸው በተጠቀሰው መሰረት በየክፍለ
የተጠኚዎቹ ቁጥር እስኪሙዋላ ድረስ ተማሪዎች በናሙናነት ተወስደዋል፡፡ ከእያንዳንዱ መማሪያ ክፍል
11 ተጠኚ በመውሰድ ጠቅላላ ብዛታቸው 122 የሆኑ ተጠኚዎች ተሳታፊ ተደርገዋል፡፡ ጥናቱ ሁሇት
የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያዎችን ተጠቅሟል፡፡ እነሱም አዳምጦ የመረዳት ፈተና እና የጽሑፍ መጠይቅ
ናቸው፡፡ የጽሁፍ መጠይቅ እና ፈተና የተጠኚዎቹ ወቅታዊ አዳምጦ የመረዳት ችሎታ ከተነሳሽነትና
አመሇካከት ጋር ያሇውን ተዛምዶ ሇመመርመር የረዱ መረጃዎችን ሇመቀበል አገልግሇዋል፡፡ የጥናቱ
ግኝት እንዳመላከተው በተጠኚዎቹ የተያዘው አጠቃላይ የአማርኛ ቋንቋ የማዳመጥ ተነሳሽነት
እስታቲስቲካዊ ልኬት (አማካይ ውጤት 3.1856) ተነሳሽነታቸው ውሱንነት የሚታይበት መሆኑን
አመላካች ሲሆን፤ በአንጻሩ አማካይ ውጤት 4.173 የሚያሳየው በተጠኚዎቹ ዘንድ የሚታየው
የማዳመጥ አመሇካከት በአጥጋቢ እና አበረታች ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን ነው፡፡ ከዚህም ጋር ገላጭ
እስታቲስቲክሱ እንዳመሇክተው አዳምጦ የመረዳት አማካይ ውጤቱ 11.75 ከማሇፊያ ማርክ 10 በላይ
በመሆኑ አብዛኞቹ ተማሪዎች አዳምጦ በመረዳት ፈተናው አጥጋቢ ነው ባይባልም መካከሇኛ
(moderate)
የሚባል ውጤት እንዳመጡ የጥናቱ ውጤት አረጋግጧል፡፡ በተተኳሪዎቹ አዳምጦ
የመረዳት ተነሳሽነትና አዳምጦ የመረዳት ችሎታ መካከል ዝቅተኛ ተገላብጧዊ (rxy -0.146) ተዛምዶ
መኖሩን ፍተሻው የቃኘ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ሁሇተኛው የተዛምዶ ልኬት (የአመሇካከት ተላውጦ)
እንደሚያመሇክተው አዳምጦ የመረዳት አመሇካከት ሲጨምር (rxy 0.540) አዳምጦ የመረዳት ችሎታም
በአንጻሩ በትይዩነት መጨመር የሚታይበት መሆኑን የጥናቱ ውጤት አረጋግጧል፡፡ በሌላ በኩል
በሁሇቱ የአመሇካከት እና አዳምጦ የመረዳት ተሇዋዋጮች መካከል የሚታየው የተዛምዶ መጠን በ0.50
እና 0.59 መካከል የሚታይ በመሆኑ አዎንታዊ መካከሇኛ ተዛምዶ መኖሩን መገንዘብ ተችሏል፡፡