Abstract:
ይህ ጥናት ያተኮረው ተግባር ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂል በማጎልበት ረገድ
ባለው አስተዋጽኦ ላይ ሲሆን፣ በጅማ ዞን ሲግሞ ወረዳ በሮቤ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘጠነኛ ክፍል
ተማሪዎችን ተተኳሪ በማድረግ የተካሄደ ነው፡፡ ይህ ጥናት መጠናዊ ሲሆን የተከተለው የአጠናን ዘዴ ከፊል
ሙከራዊ ጥናታዊ ንድፍ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ሁለት የ9ኛ ክፍሎች ተማሪዎችን በቀላል እጣ ናሙና ዘዴ
በመምረጥና ቅድመ-ትምህርት ፈተና በማቅረብ ከየክፍሉ ተማሪዎች መካከል የተሻለና ተቀራራቢ አንቀጽ
የመጻፍ ችሎታ ያላቸውን 50 /ሃምሳ/ ተማሪዎች በመለየት፤ የአንዱን መማሪያ ክፍል 50 ተማሪዎች የሙከራ
ቡድን፣ የሁለተኛውን መማሪያ ክፍል 50 ተማሪዎች የቁጥጥር ቡድን ተጠኚዎች ተደርገዋል፡፡ በቅድመ ትምህርቱ ፈተና ሁለቱ ቡድኖች በመነሻ ደረጃ በተለያዩ ማስተማሪያ ዘዴዎች ከመማራቸው አስቀድሞ
በድርሰት መጻፍ መሰረታዊ ግንዛቤያቸው ጉልህ ልዩነት እንደሌላቸው ታውቆ በሙከራ ጥናቱ ተሳትፈዋል፡፡
የሙከራውን ቡድን በተግባር ተኮር ማስተማሪያ ዘዴ፣ የቁጥጥር ቡድኑን በልማዳዊ ዘዴ ለስምንት ሳምንታት
አንቀጽ የመጻፍ ልምምድ እንዲያካሂዱ በማድረግ፣ በቅድመ-ትምህርትና በድህረ-ትምህርት ከቁጥጥርና
የሙከራ ቡድኖቹ በአንቀጽ መጻፍ ላይ ያተኮረ የፈተና መረጃ ተሰብስቦ በሶስት የአማርኛ ቋንቋ መምህራን
በማረም የፈተናዎቹ አማካይ ውጤቶች በገላጭና ድምዳሜያዊ ስታቲስቲክስ (በነጻ ናሙናዎች ቲ-ቴስት እና
ፒርሰን የተዛምዶ ልኬት ተተንትነዋል፡፡ እንዲሁም ከሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች በቅድመ እና ድህረ ትምህርት የአንቀጽ መጻፍ ተነሳሽነት የጽሁፍ መጠይቅ ምላሽ አማካይ ውጤቶች በገላጭና ድምዳሜያዊ
ስታትስቲክስ (በዳግም ልኬት ናሙናዎች ቲ-ቴስት) ትንተናና ማብራሪያ ተካሂዶባቸዋል፡፡ የጥናቱ ግኝቶች
እንዳመለከቱት፣ የሙከራው ቡድን በተግባራት የታገዘ አንቀጽ የመጻፍ ልምምድ እድል በማግኘቱ
ያስመዘገበው የድህረ-ትምህርት ፈተና ውጤት በተለመደው ዘዴ አንቀጽ መጻፍ ሲማር ከቆየው የቁጥጥር
ቡድን የድህረ-ትምህርት ፈተና ውጤት እንዲሁም ከራሱ ከሙከራ ቡድኑ የቅድመ-ትምህርት አንቀጽ
የመጻፍ አማካይ ውጤት ጉልህ ልዩነት ማሳየቱን ውጤቱ (t= 5.340, df= 49, p= 0.000) የባለ ሁለት ጫፍ
የጉልህነት ውጤት አመላክቷል፡፡ በ49 የነፃነት ደረጃ (degree of freedom) የባለሁለት ጫፍ ጉልህነት ዋጋ
(p<0.05) ሲሆን የተገኘው የባእድ ናሙና ቲ-ቴስት ዋጋ ከ0.05 አንሶ ተገኝቷል፡፡ በዚሁ መሰረት ተግባር
ተኮር የቋንቋ ማስተማሪያ ዘዴ በሂደታዊ የመጻፍ ተግባራትና ተግባቦታዊ ክንውኖች የተደገፈ በመሆኑ
የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የመጻፍ ክሂልን በማጎልበት ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ተረጋግጧል፡፡
በሌላ በኩል የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች በድህረ-ትምህርት የአንቀጽ መጻፍ ተነሳሽነት የጽሁፍ መጠይቅ
ጥቅል ምላሽ አማካይ ውጤት ከቅድመ-ትምህርቱ ምላሻቸው አማካይ ውጤት ሲነጻጸር ለውጡ መካከለኛ
(moderate) የጉልህነት ደረጃ ላይ መገኘቱን ውጤቱ (t= -16.652, df= 49, p= 0.077) አመላክቷል፡፡ ይህም
የሚያመለክተው በ49 የነፃነት ደረጃ (degree of freedom) የባለሁለት ጫፍ ጉልህነት ዋጋ (p<0.05) ሲሆን
የተገኘው የባእድ ናሙና ቲ-ቴስት ዋጋ ከ0.05 አንሶ ሳይሆን ወደ0.05 የተጠጋ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከቀረቡት
የተግባር ተኮር የተነሳሽነት መለኪያ ተላውጦዎች (የተግባር አጠቃላይ ግንዛቤ፣ ተራክቦአዊ ተግባራት እና
ተቀባይነት ያለው ውጤት የማቅረብ ክንውኖች) መካከል፣ ለ‹ተቀባይነት ያለው ውጤት የማቅረብ ክንውን›
ያሳዩት የተነሳሽነት ለውጥ ልዩነት የጉልህነት ደረጃ ያነሰ /ዝቅተኛ/ መሆ