Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በምስራቅ ወለጋ ዞን በአርጆ ወረዳ የሚገኙት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
ቤቶች የምያስተምሩ የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የትምህርት መርጃ መሣርያዎች አጠቃቀም
በጠቅላይ ናሙና በመጠቀም መፈተሽ ነው፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም አይነታዊና መጠናዊ
የምርምር ዜደ ተግባራዊ ሆኗል፡፡ የጥናቱ ተሳታፉዎችም በአርጆ ሁለተኛ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ
ዘጠኝ የአማርኛ ቋኝቋ መምህራን እና አንድ የትምህርት ቤቶቹ ሱፐርቨይዘር ያሳተፈ ነበር፡፡
መረጃዎቹ የተሰበሰቡትም በክፍል ዉስጥ ምልከታ ፣በቃለ መጠቅእና በውይይውት መረጃዎችን
በመሰብሰብ በገላጭ ምርምር ስልት ተተንትነዋል፡፡ የጥናቱ ግኝትም በቂ የሆነ ሥልጠና
ባለማግኘታቸው በአጠቃቀም ረገድ ያላቸው ተሳትፎ አናሳ መሆን፣በአብዛኛው ያለ መርጃ መሣርያ
ማስተማራቸው፣የተጠቀሙት የትምህርት መርጃ መሣርያ ጉል ሆኖ አለመገኘት፣ሳብ
እንዳልሆነ፣ተሰማም እዳልሆነ፣በመጠኑ የተጠቀሙት እይታዊ ብቻ መሆኑ፣ለተጠቀሙትም ተገቢ
ማስቀመጫ ቦታ እንደለላቸው፣ የተገኙትም የትምህርት መርጃ መሳረያዎች በመምህራን
አሰተባባርነት በተማሪዎች የተሠሩ መሆን እና ተጠኝዎቹ የትምህርት መርጃ መሳርያ ለማዘጋጀት
በቂ ዕውቀት፣ ፍላጎትና ልምድ እንደለላቸው በጥናቱ ምልከታ ወቅት ለማረጋገጥ ተችለዋል፡፡
የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መሣሪያዎች ከተማሪው መማሪያ መጽሐፍ ውጭ ሌሎች እንደሌሉ
ተረጋግጧል፡፡ በመሆኑም የመንፈቀ ዓመት ዕቅዳቸው ከመርሓ ትምህርቱ ጋር የየትምህርት ቤቶቹ
እቅዶች የቅርፅና የይዘት ልዩነት ታይተዋል፡፡ ትንተናውም መረጃዎቹ በሚያነሱት ጉዳይ ተከፋፍሎ
በሠንጠረዥ ውስጥ በቁጥርና በመቶኛ ስሌት (%) በማስቀመጥ በምስራቅ ወለጋ ዞን፣በአርጆ ወረዳ
ካሉት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአማርኛ ቋንቋ መምህራን የትምህርት መርጃ መሣርያ
አጠቃቀም ሁነታ አጥኝው ጠቁመዋል፡፡ መመጨረሻም ለእነዚህ እንቅፋቶችም በኦሮሚያ
ትምህርት ቢሮ፣ በመምህራን ትምህርት ኮለጅ ደረጃ፣ በትምህርት ቤት ደረጃና የሚመለከተው
አካላት ምን ማዲረግ እንደሚገባቸው የመፌትሄ ሀሳቦች ተጠቁመዋል፡፡