Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና አለማ በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በወሊድ ስርዓተ ከበራ ላይ የሚነገሩ
የቃል ግጥሞች ይዘትና ማህበራዊ ፋይዳ ትንተና ማድረግ ነዉ፡፡ የጥናቱ ዋና ትኩረት አላማ ማህበረሰቡ
የወሊድ የቃል ግጥም ክዋኔዎች በተክኖሎጂ እድገት ሰበብ ሙሉ በሙሉ ሳይጠፋ መረጃዉን ለቀጣዩ
ትዉልድ በፅሁፍ ተሰንዶ እንድቀመጥ ማድረግ ነዉ ፡፡
የጥናቱ መረጃ የተሰበሰዉ ቀዳማይ መረጃ ምንጮች እና ከከልአይ የመረጃ ምንጮች ናቸዉ፡፡ አንዲት
ሴት ፅንስ ከተፀነሰ በኋላ ከነፍሰ ጡር ጋር ትቀላቀለለች ፤ ነፍሰ ጡር ካልሆኑት ትለያለች፤ ፅንሱ እስከ
አንድ ወር ሲሆናት ሽግግር ላይ ትገኛለች፤ ሴትዬዋ ምጥ ስይዛት ሽግግር ላይ ስትሆን ስትወልድ ከወላድ
ጋር ትቀላቀለለች ፤ ከነፍሰጡር ትነጠላለች፤ ህፃኑ ሲወለድ ሽግግር ላይ ነዉ፡፡ የሸነኒ እለት የተወለደዉ
ህጻን/ኗ ከሌሎች ህፃናት ጋር ይቀላቀላል/ትቀላቀላለች ፡፡ ሴትዬዋ ከወሊድ በኋላ ከሚያጠቡት ጋር
ትቀለቀለለች ፡፡ ወላድ ሴትም ገለዋን የታጠበች ቀን ከማህበረሰቡ ጋር ትቀለቀለለች፡፡
ወሊድ ስርዓተ ክወና ለህብረተሰቡ መተሳሰብን፣ መረዳዳትን፣ አንድነትን፣ ፍቅርን፣ መተዛዘንን፣ አብሮ
መደሰትን ለግለሰቡም ሆነ ለማህበረሰቡ ከፍተኛ ጠቀሜታ ስለለዉ ለትዉልድ ቀጣይነት እንድኖረዉ
ያደርገዋል፡፡ በወሊድ ስነ ስርዓት ላይ የሚፈጸሙት ሀገረሰባዊ እምነቶች ትዕምርታዊ ጉዳዮች የማህበረሰቡን
ምኞት፣ ፍልስፍና፣ እንዱሁም ባህልና እሴታቸውን የሚገጹበት መንገድ የማህበረሰቡን ህልውና አስጠብቆ
መቆየት ያስቻለ ከመሆኑም በላይ ማህበራዊ ፊይዳ እና ስነ ልቦናዊ ፊይዳ እንደሚያገኙበት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡