Jimma University Open access Institutional Repository

የግራኝነት እምነታዊና ማህበራዊ ፍልስፍና ትንተና በካፋ ብሔረሰብ ተተኳሪነት

Show simple item record

dc.contributor.author ሰለሞን ወንድሙ ገብሬ
dc.contributor.author ለማ ንጋቱ
dc.contributor.author ጥበቡ ሽቴ
dc.date.accessioned 2025-06-17T08:07:52Z
dc.date.available 2025-06-17T08:07:52Z
dc.date.issued 2024-04-06
dc.identifier.uri https://repository.ju.edu.et//handle/123456789/9605
dc.description.abstract የዚህ ጥናት አቢይ ዓላማ ‹‹ግራኝነት በካፋ ብሔረሰብ ዘንድ ያለውን ማህበራዊ ፍልስፍና (ትዕምርትነት) መተንተን›› ነው፡፡ የጥናቱ ዘዴ አይታዊ ሲሆን የመተንተኛ ስልቱ ደግሞ ገላጭ ትዕምርታዊ ፍከራን የተከተለ ነው፡፡ በታላሚና በጠቋሚ ከተመረጡ መረጃ አቀባዮች አስፈላጊውን መረጃ በቃለመጠይቅና በሰነድ ፍተሻ፤ መቅረፀ ድምፅና ማስታወሻ ደብተር መረጃ መቅረጫ መሳሪያዎችን በመጠቀም መረጃው ተሰብስቧል፡፡ ጥናቱ በካፋ ብሔረሰብ በቦንጋ ዙሪያ፣ በጠሎ እና ዴቻ ወረዳዎች ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ የተሰራ ነው፡፡ ከመስክ የተሰበሰበው መረጃ ላይ በተደረገው ትንተናም መሰረት ግራኝነት የሰይጣንነት፣ የክፋት፣ የስግብግብነት ወይም የአልጠግብ ባይነት እንዲሁም በብሔረሰቡ ዘንድ በሚታመኑ ሀገረሰባዊ ዕምነቶች አንፃር የእርኩስነት ትዕምርትነት ያለው መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ሚት ውስጥ ግራኝነት የሰይጣን፤ በተረት ውስጥ ግራ የስውር ተንኮል፣ በምሳሌያዊ አነጋገር ውስጥ የአቅመቢስነት ወይም የአለመታመንና የርኩስ ወይም የመናቅ እንዲሁም በፈሊጣዊ አነጋገር ውስጥ ደግሞ በኢ-ፍትሃዊነት ትዕምርትነት መቅረቡ ተገልጿል፤ ማህበረሰቡ ግራኝነትን በመጥፎ ተምሳሌትነት ወይም ትዕምርትነት እንዲወክል ተፅዕኖ እንዲኖር በዋናነት ያስቻሉት ስነቃዊ እሴቶችና የሀገረሰባዊ ዕምነት አስተምህሮ ተፅዕኖዎች እንደሆኑ፤ ህፃናት ግራኝ እንዳይሆኑ ጥብቅ ክትትልና ግራኝ ከሆኑ የከፋ ቅጣት እስከማስከተል እንደሚደርስ፣ ቅጣቱ በታደጊዎች ስነልቦና ላይ የሚያሳድረው ጫና ቀላል አለመሆኑና በተዛማጅ ጥናት ላይ የተዳሰሱ ጥናቶች ከስነቃል፣ ከሀገረሰባዊ ዕምነት ትዕምርትነት አንፃር ያልዳሰሱትን ጉዳዮች ወይም ክፍተቶች ለመሙላት የሚያስችሉ ነጥቦችን አመላክቷል፡፡ en_US
dc.language.iso other en_US
dc.title የግራኝነት እምነታዊና ማህበራዊ ፍልስፍና ትንተና በካፋ ብሔረሰብ ተተኳሪነት en_US
dc.type Thesis en_US


Files in this item

This item appears in the following Collection(s)

Show simple item record

Search IR


Browse

My Account