Abstract:
የጥናቱ ዋና ዓላማ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መፃህፍት ውስጥ
የተካተቱ የተውሶ ቃላት አቻዊነት ቅርጽና መዋቅር ትንተና በሚል የተካሄደ ነው፡፡
አጥኚው የጥናቱን መረጃ በማሰባሰብ በዋናነት የሰነድ ፍተሻ ዘዴ የተጠቀመ ሲሆን ከሰነድ
የተሰበሰቡ መረጃዎችን በወካይ ናሙና የተመረጡትን ቃላት ለመተንተን አይነታዊ ዘዴን
ተጠቅሞ መረጃዎችን በገለፃ ተተንትነው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በመረጃ ትንተናው
መሰረት በመማሪያ መጻህፍት የተከናወነው ተውሰት፣ የውሰት አይነቶችን መሰረት ያደረገ
ነው፡፡ በሰዋስዋዊ ባህሪና አውዳዊ አገባብ የቅርጽ ለውጥ በማድረጋቸው ከመገኛቸው ጋር
ተዛምዶ የላቸውም፡፡ በውሰት የተካተቱ ቃላት የታላሚውን ቋንቋ የእርባታ ስርዓት
በመከተላቸው ከአዋሹ ቋንቋ የእርባታ ስርዓት ጋር ተዛምዶ የላቸውም፡፡ ነባር ቃላትን
ጠብቆ ለማቆየት፣ የታላሚ ይዘቶች በአንድ ላይ መካተታቸው በመማሪያ መፃህፍት
መግቢያ ላይ ከተገለጹት ዓላማዎች አኳያ በመርሐ ትምህርት ላይ ግልጽ የሆነ መረዳትና
ትክክለኛ መዋቅራዊ አቀራረብ የሌለው ነው ማለት ይቻላል፡፡ በመሆኑም የቋንቋ መማሪያ
ዝግጅት የአዘጋጆቹን የዕውቀት ደረጃ መሰረት ያደረገ መሆን ስላለበት የተማሪውን ዳራ
እና አቀባበል ያማከለ ዝግጅትና አቀራረብ ያስፈልገዋል፡