Abstract:
የዚህ ጥናት ዓላማ የAማርኛን ቋንቋ መምህራን የጽህፈት ስህተት Eርማት Eና ምጋቤ
ምላሽ መፈተሽ ነው፡፡ ተጠኚዎች በጅማ ከተማ የሚገኙ የጅሬን፣ የመወዳና የጅማ
ዩኒቨርስቲ ኮሚዩኒቲ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2009 ዓ.ም የ9ኛ ክፍል
ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩና በተራ የEጣ ናሙና ዘዴ የተመረጡ 426
ተማሪዎችና በAጠቃላይ ናሙና የተወሰዱ በሦስቱ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የ9ኛ ክፍል
የAማርኛን ቋንቋ የሚያስተምሩ ሰባት መምህራን ናቸው፡፡ የጥናቱ መረጃ የተሰበሰበው
በሰነድ ፍተሻ፣ በጽሁፍ መጠይቅና በቃለ መጠይቅ ነው፡፡የተሰበሰቡት መረጃዎች
የተኮሩት በመምህራን የታረሙ የተማሪዎች ደብተር፣ የፈተና ወረቀቶች Eና
በተማሪዎች የተፃፉ ድርሰቶች ናቸው ሲሆኑ የAማርኛ ቋንቋ መምህራን የጽሁፍ
ስህተት Eርማትና ምጋቤ ምላሽ ምን Eንደሚመስል ተተንትኗል፡፡
በመጨረሻም የAማርኛ ቋንቋ መምህራን የተማሪዎችን የጽሁፍ ስህተት ማረም
Aለማረማቸው፣ የAማርኛ ቋንቋ መምህራን የጽህፈት ስህተት Eርማት ዘዴ Eና
የAማርኛ ቋንቋ መምህራን ተማሪዎች ከሚፈጽሙት የጽህፈት ስህተቶች የትኛው ላይ
Aትኩረው Eንደሚያርሙ ተመልክቷል፡፡ በዚህም መሰረት የAማርኛ ቋንቋ መምህራን
የተማሪዎችን ስህተት Eንደማያርሙ በጥናቱ ተረጋግጧል፡፡ ከጥናቱ ውጤት በመነሳት
የተማሪዎችን የጽህፈት ስሕተት ማረም ለተማሪዎች የጽህፈት ችሎታ ወሳኝ በመሆኑ
የAማርኛ ቋንቋ መምህራን የተማሪዎችን የጽህፈት ስህተት በንድፈ ሃሳብ ላይ
ተመስርተው ቢያርሙ የተሻለ ነው የሚል Aስተያየት ተሰጥቷል፡፡