Abstract:
የጥናቱ ዋና አላማ በበላይ ዘለቀ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች
የማጠቃለል ብልሀት ለአንብቦ መረዳት ችሎታ ያለውን ፋይዳ መመርመር ነ ው፡ ፡ የጥናቱ ንድፍ ከፊል ሙከራዊ
ነ ው፡ ፡ የጥናቱ ተሳታፊዎች በምስራቅ ጎጃም በብቸና ከተማ በበላይ ዘለቀ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤት በ2011 ዓ.ም በ9ኛ የክፍል ደረጃ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ከሚገ ኙት 915
ተማሪዎች መካከል በእድል ሰጪናሙና ዘዴ የተመረጡ 60 የቁጥጥር ቡድንና 58 የሙከራ ቡድን በድምሩ
118 ተማሪዎች ናቸው፡ ፡ ከእነ ርሱም በፈተናና በፅሁፍ መጠይቅ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች
ተሰብስበዋል፡ ፡ የተሰበሰቡት መረጃዎች በዳግሞ ልኬት ናሙና ቲ-ቴስትና በነ ጻ ናሙና ቲቲስት ተሰልተው
በገ ላጭና ድምዳሜያዊ ስታቲስቲክስ ተተንትነ ዋል፡ ፡ በውጤት ትንተናው መሰረት የሙከራ ቡድኑ የድህረ
v
ትምህርት ፈተና ቡድን አማካይ ውጤት በስታቲስቲክስ ጉልህ ልዩነ ት (p<0.05) ታይቷል፡ ፡ ይህም
የሙከራ ቡድን ተማሪዎች የማጠቃለል ብልሀትን ብቻ በመማራቸው የማጠቃለል ብልሀት በአንብቦ መረዳት ችሎታ
የተሻሉ መሆናቸውን በጉልህ አመላክቷል፡ ፡ በቅድመ ትምህርትና ድህረ ትምህርት የሚማሩ የቁጥጥር ቡድን
ተማሪዎች አማካይ ውጤት መካከልም በስታትስቲክስ ጉልህ የሆነ ልዩነ ት (p>0.05) አላሳየም፡ ፡ በዚህም
መሰረት የቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች በማጠቃለል ብልሀት አንብቦ መረዳት ችሎታ ከሙከራ ቡድን የተሻሉ
አለመሆኑ በጥናቱ ተረጋግጧል፡ ፡ ይህም የሆነ ው የሙከራ ቡድን ተማሪዎች ምንባብን በሚማሩበት ጊዜ
የማጠቃለል ብልሀትን ብቻ በመማራቸውነ ው፡