Abstract:
ይህ ጥናት ሂደተ ዘውጋዊ የመፃፍ ማስተማሪያ ዘዴ የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂልን
በማሻሻል ረገድ ያለውን ውጤታማነት ፈትሽዋል፡፡ ጥናቱም ተተኳሪ አድርጎ የተካሄደው
በኦሮሚያ ክልል በጂማ ዞን በሠቃ ጮቆርሳ ወረዳ በሚገኘው ሠቃ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
በ2011 ዓ.ም በሚማሩ በ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ላይ ነው፡፡ ጥናቱም በፍትነታዊ ሙከራ ዘዴ
ተማሪዎችን በቁጥጥር እና በሙከራ ቡድን ሁለት ክፍሎችን በመውሰድ ተካሂዷል፡፡
መረጃዎችም በፈተና እና በምልከታ የመረጃ መሰብሰብያ ዘዴዎች ተሰብስበዋል፡፡
በተደረገው አተገባበራዊ ክንውን የተገኘው መረጃ በመጠናዊና በአይነታዊ ዘዴን
በመመስረት በገላጭ እስታቲክስ ስልት ተተንትነዋል፡፡ የተገኘውም ውጤት
እንደሚያመለክተው በሂደታዊ ዘውግ የተማሩት የሙከራ ቡድኑ ተማሪዎች በልማዳዊው
(በመርሃ ትምህርቱ) ከተማሩት የቁጥጥር ቡድን ተማሪዎች በተሻለ የመጻፍ ክሂላቸው
እንደተሻሻለ፣ በቂ ደረጃ ላይ እንደደረሰ፣ የመጻፍ ተሳትፎዋቸው እንደተሸሻለ፣ በመጻፍ
እንደተደሰቱና የመጻፍ ጭንቀታቸው መካከለኛ መሆኑን አመልክቷል፡፡ በመሆኑም ሂደታዊ
ዘውግ የመፃፍ ማስተማሪያ ዘዴን በመጠቀም የተማሪዎችን የመጻፍ ክሂልን ማሻሻል፣ በቂ
ደረጃ ላይ ማድረስ፣ ተሳትፎቸውን መጨመር፣ የመጻፍን ተግባር ደስተኛ ማድረግ እና
የመጻፍን ጭንቀት በመቀነስ ተማሪዎችን ለደረጃቸው የሚመጥን የመጻፍ ክሂል ችሎታ ላይ
ማድረስ ይቻላል የሚል አስተያየት ላይ ተደርሷል፡፡