Abstract:
ይህ ጥናት በላይ ጋይንት ወረዳ የተቃዉሞ ቃል ግጥም ማህበራዊ ፋይዳ እና አንድምታ
ማሳየት በሚል ዋና ዓላማ የቀረበ ነው። ጥናቱ የተሳካ ይሆን ዘንድ ጽሁፋዊ ማስረጃዎችን
ከመጠቀም በተጨማሪ በቃለ መጠይቅ፣ በምልከታ፣ በቡድን ተኮር ውይይት መረጃዎች
ተሰብስበዋል። የተሰበሰቡ መረጃዎችም በማስታዎሻ፣ በምስል፣ በመቅረጸ ድምጽ እና
እንደአስፈላጊነቱ በቪዲዮ ካሜራ በማጠናቀር መረጃዎቹን መሰብሰብ ተችሏል። እነዚህ
የተቃዉሞ ቃል ግጥሞች ገላጭ የምርምር ዘዴ በመጠቀም መረጃዎች ተተንትነዋል።
እንዲሁም የተጠኝ አካባቢና የማህበረሰቡ ዳራዊ ገለጻ ተቃኝቷል። በመሆኑም
የተሰበሰቡትን የተቃዉሞ ቃል ግጥሞች ከይዘታቸው አንጻር አስተዳደራዊ ችግሮችን፣
የመሬት ኢ-ፍትሃዊ ክፍፍል፣ አድሎአዊነትን የሚጠቁሙ ሆነዉ ተገኝተዋል። ከፖለቲካ
ልዩነቶች አንጻር ማህበረሰቡ የሚጠላዉንና የሚወደዉን አመላካች ሃሳቦች የተንጸባረቁባቸዉ
ሆነዉ ተገኝተዋል። ስለዚህ የዚህን ጥናት ዉጤት መሰረት በማድረግ የአካባቢዉን
ማህበረሰብ ለመለወጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የተቃዉሞ ቃል ግጥሞቹን በመረጃነት
መጠቀም ቢቻል ጥሩ ነዉ።