Abstract:
የዚህ ጥናት ዋና አላማ የመማር ተነሣሽነት ከአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር ያለውን ተዛምዶ በ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ተተኳሪነት መፈተሽ ነው፡፡ የጥናቱን አላማ ለማሳካትም ተዛምዷዊ የምርምር ስልት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ጥናቱ በአመቺ የንሞና ዘዴ በተመረጠ በሁሩሙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተካሄደ ነው፡፡በተጨማሪም የ10ኛ ክፍልን በአላማ ተኮር የንሞና ዘዴ በመጠቀም የዚህ ጥናት ተተኳሪዎች ሆነዋል፡፡ የጥናቱ ተሳታፊዎችም በእኩል እድል ሰጪ የንሞና ዘዴ የተመረጡ 97 የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው፡፡ የመማር ተነሳሽነታቸው አማካይ ውጤት 3.027 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የተማሪዎቹ የመማር ተነሣሽነት መደበኛ ልይይት0.36814 ሲሆን የእያንዳድ ተጠኚ ምላሽ አማካይ ውጤት ርቀቱ ጠባብና የማያዋዥቅ ሲሆን ተማሪዎች ከውስጣዊ ተነሣሽነት የበለጠ ለውጫዊ ተነሣሽነት ትኩረት የሰጡ ሲሆን ጉልህ ልዩነት ግን እንደሌለ በባድ ናሙና ፍተሻ ተረጋግጧል፡፡ ዉጤቱም 0.76 ሆኖ ተመዝገቧል፡፡ የተማሪዎቹ አንብቦ መረዳት ችሎታ በአማካይ ውጤታቸው ተሰልቷል፡፡ በተማሪዎች የመማር ተነሣሽነትና በአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በእስታቲክስ፣ በፒርሰን የተዛምዶ መለኪያ ተሰልቷል፡፡ የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየውም የተማሪዎቹ አንብቦ መረዳት ችሎታ አማካይ ውጤት(53.938) መሆኑ በናሙና ፍተሻ ተረጋግጧል፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ የአንብቦ መረዳት ችሎታ አለ ለማለት አያስደፍርም፡፡ በመማር ተነሳሽነትና በአንብቦ መረዳት ፈተና ውጤት መካከልም አዉነታዊ ተዛምዶ አልታየም፡፡ ውጤቱም (r= -049 የ"P" ዋጋ 0.852 ወይም P > 0.5) በመሆኑ አሉታዊ ተዛምዶ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡